🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ውስጥ እና መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ። ወዳጄ A:-መንፈስ ቅዱስ #በእ | GOD'S GOSPEL

መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ውስጥ እና መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ።


ወዳጄ A:-መንፈስ ቅዱስ #በእኛ_ውስጥ የለም እንደ ቆይ??
እኔ:-አለ! ዳግም ስለተወለድን #በእኛ_ውስጥ አለ።
ወዳጄ A:-ታዲያ ለምንድነው ወንጌል ስንሰብክ በእኛ #ድንቆች፣ #ተዓምራቶች እና #ምልክቶች የማይደረጉት??

እኔ:-የመንፈስ ቅዱስ #በአንተ_ውስጥ መሆን እና የመንፈስ ቅዱስ #በአንተ_ላይ መሆን ይለያያል።

የመንፈስ ቅዱስ በአንተ ውስጥ መሆን #ለአንተ ሲሆን የመንፈስ ቅዱስ በአንተ ላይ መሆን #ለሌሎች ነው።
መንፈስ ቅዱስ በአንተ ውስጥ የሚሆነው በጌታ አምነህ ስትድን መንፈስህ ዳግም ሲወለድ ነው። የእርሱ(የመንፈስ ቅዱስ) በአንተ ውስጥ መሆኑም ለጽድቅ፣ ለደህንነት፣ ለቅድስና፣ እግዚአብሔርን ለመምሰል እና ከሀጥያት የበላይ የሆነን ህይወት ለማኖር ነው።(#ለአንተ_ጥቅም ነው)
የመንፈስ ቅዱስ በአንተ ላይ መሆን ግን ለድሆች ወንጌልን፣ ለታሰሩት መፈታትን፣ለዕውሮች ማየትን፣ ለተጠቁት ነጻ መውጣትን፣ ለታመሙ ፈውስን ትሰብክ ዘንድ ነው።(#ለሌሎች_ጥቅም ነው)

የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ #በእኔ_ላይ ነው፥ #ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ #ለተማረኩትም ነጻነትን #ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛል።”
ኢሳይያስ 61፥1

 ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ #በእናንተ_ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ #ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ።—ሐዋርያት 1፥8

The Spirit of God in you is #for_you; the Spirit of God up on you is #for_others(It will make you heal the sick,deliver the captives,recover the sight to the blind,do miracles & wonders and raise the dead).

Share it
Join @Godsgospel
@Godsgospel