Get Mystery Box with random crypto!

የሮሜ መጽሐፍ ጥናት: ከምዕራፍ አንድ ጀምሮ እስከአሁን የተመለከትናቸው ዋና ዋና ትምህርቶች። ሮሜ | GOD'S GOSPEL

የሮሜ መጽሐፍ ጥናት:
ከምዕራፍ አንድ ጀምሮ እስከአሁን የተመለከትናቸው ዋና ዋና ትምህርቶች።

ሮሜ 1፥1-16 --- ጳውሎስ ማነው? ---ወንጌል ምንድነው?---በሮም ያሉ ክርስቲያኖች ምን ይመስላሉ?--- በመጀመሪያዎቹ አስራ ስድስት ቁጥሮች ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ተሰጥቷል።

ሮሜ 1፥17-32 --- የሰው ዘር ሁሉ ውድቀት--- እግዚአብሔር ለሰዎች ሁሉ የገለጠው የራሱ መገለጥ *አምላክነቱ እና ዘላለማዊ ሃይሉ* ---የሰዎች እንቢተኝነት---ለእግዚአብሔር ክብርን አለማቅረብ እና ምስጋናን አለመስጠት---የሰዎች እንቢተኝነት ውጤት ---በመጀመሪያ ሁለት ውጤቶች የጣዖት አምልኮና ቅዱስ ያልሆነ ሩካቤ ስጋ---በመቀጠል ለማይረባ አእምሮ ታልፎ መሰጠት--- ውጤቱ በሁሉም አይነት ክፋት መሞላት/21 ክፉ ባሕሪያት ተዘርዝረዋል/። የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ ውጤቶች በቀዳሚነት ስጋን የሚያረክሱ ስሆን የቀጠለው ውጤት ደግሞ አእምሮንም የሚያረክስ ነው።

ሮሜ 2፥1-16 ---አምስት የእግዚአብሔር ፍርድ መርሆች---እውነት፣ ስራ፣ አድሎ አልባነት፣ ብርሃን(እውቀት)፣ በሰዎች ልብ የተሰወረ ሚስጥር---በተጨማሪም የእግዚአብሔር ፍርድ የማይመረመር እና ከሰዎች አእምሮ የበለጠ ነው ሮሜ 11፥28---

ሮሜ 2፥17-29 --- የኃይማኖተኛ ሰዎች በደል---በምሳሌነት የቀረቡት አይሁድ ናቸው። የአይሁድ ኃጢአት ምንድነው? ---ከእግዚአብሔር ሕግን ቢቀበሉም መጠበቅ አልቻሉም---በተጨማሪም ኃይማኖተኛ ሰዎች የሚያደርጓቸው ውጫዊ ስርዓቶች ሰዎችን ለማጽደቅ ዋጋ የሚኖራቸው አይደሉም ---በተጻፈ ሕግና ግዝረት አይሁድ በእግዚአብሔር ፊት መጽደቅ አልቻሉም።

ሮሜ 3፥1-7 ---ይሁዲ የመሆን ብልጫው እና የመገረዝ ጥቅሙ በብዙ መልኩ ብዙ ነው---በመጀመሪያ ይሁዲዎች ናቸው የእግዚአብሔር ቃል በአደራ የተሰጣቸው ---አይሁድ ለተቀበሉት ቃል ታማኞች ባለመሆናቸው እግዚአብሔር ታማኝነቱን አይለውጥም---በአይሁድ እምቢተኝነት የእግዚአብሔር ጽድቅ የበለጠ ጎልቶ ታይቷል--- የአይሁድ እምቢተኝነት የእግዚአብሔር ታማኝነት የሚያጎላ ቢሆንም እግዚአብሔር ግን እውነተኛ በመሆኑ ፍርዱ የማይቀር ነው።

ሮሜ 3፥9-20 ---አይሁድም ሆኑ አሕዛብ ከኃጢአት በታች በመሆናቸው መበላለጥ የለም---በድጋሚ የሰዎች ውድቀት ከብሉይ መጽሐፍት በመጥቀስ ተብራርቷል---ሁሉም ተሳስተዋል የሚለው ሐረግ የሰውን ዘር ሁሉ የሚመለከት ነው---የብሉይ መጽሐፍት ግን የተጻፉት ለአይሁድ ስለሆነ የሰዎችን ኃጢአተኝነት የሚገልጸው የመዝሙር ክፍል በቀዳሚነት ይሁዲን የሚመለከት ነው (ሕግ የሚናገረው ሕጉ ለተሰጣቸው ነው)-- ሕግ የተሰጠው ዓለምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች ለማድረግ ነው ሌላው ደግሞ የኃጢአት ምንነት እንድታውቅ ነው---በመጨረሻም ማንም ሰው ሕግን በመጠበቅ በእግዚአብሔር ፊት መጽደቅ አይችልም።

@TheDeepThingsOfGod
@TheDeepThingsOfGod