Get Mystery Box with random crypto!

ሐምሌ 18 / #Emotional_intelligence / #NLP የስሜት ብስለት ኑ አብረን እንማር | Hana Hailu

ሐምሌ 18 / #Emotional_intelligence / #NLP
የስሜት ብስለት
ኑ አብረን እንማር
“ስሜታዊ ነበርኩ”፤ “በስሜት የተናገርኩትን ኣላውቅም”፤ “በስሜታዊነት ነው ያደረኩት” ። እነዚህ ንግግሮች ለአብዛኞቻችን የተለመዱ ናችው። ነገር ግን ስሜቶቻችንን መረዳት እና መግዛት በመለማመድ ህይወታችንን መግራት እንችላለን።

የሰው ልጅ ከውልደቱ ጀምሮ ከራሱ፣ ከቤተሰቡ እና ከአካባቢው ጋር የሚግባበት አንዱ መንገድ ስሜት ነው። ስለዚህ ስሜት ቀዳሚው የተፈጥሮ የመግባቢያ መንገዳችን ነው። በእድሜ ከፍ እያልን ስንመጣ ብዙ ውሳኔዎችን ለመወሠን ስሜታችንን እንጠቀማለን። ነገር ግን አብዛኛውን ግዜ ስሜትን መረዳት እና መግራት የምንችልበት ጥበብ ልምምድ ስለሌለን ውሳኔያችን እና ድርጊታችን ፀፀት ይበዛዋል።

ኒውሮ ሊንጉስቲክ ፕሮግራሚንግ ስሜትን መረዳት ፤በምንፈልገው መልኩ መግራት እና ለምንፈልገው አላማ መጠቀም የምንችልባቸውን ሀሳቦችን እንድናውቅ እንዲሁም ልምምድ እንድናደርግ ጠንካራ ቴክኒኮችን ያስተምረናል።

እነዚህን የሃሳብና የስሜት መግራት ቴክኒኮች ለመማር እና ለመለማመድ፡

ሐምሌ 18 የሚጀምረውንና በኒውሮ ሊንጉስቲዊክ ፕሮግራሚንግ ስልት የተቀረፀውን ሠባተኛውን በአዲስ አበባ በአካል የምናካሂደውን ስልጠና ለመካፈል በስልክ ወይም በቴሌግራም ቁጥር +251974046870(ሀና) ይደውሉ አሊያም ስምዎን ቴክስት ያድርጉ።

ስለ NLP እና የልባም ሕይወት ፕሮግራሞች የበለጠ ለማወቅ፡

ዩቲዩብ፡

(ልባም ሕይወት ፕሮግራሞች ይዘት)

ዩቲዩብ፡

(ኒውሮ ሎጂካል ሌቭልስ ኦፍ ቼንጅ)

ቴሌግራም፡ https://t.me/libamhiwot