Get Mystery Box with random crypto!

Hawora Clinic 'ከእያንዳንዱ ስኬታማ ወንድ በስተጀርባ አንድ ጠንካራ ሴት አለች' ይህም | Hawhora Clinic-Hosanna

Hawora Clinic

"ከእያንዳንዱ ስኬታማ ወንድ በስተጀርባ አንድ ጠንካራ ሴት አለች"

ይህም የሴቶችን አስተዋጽኦ ጉልህ አድርጎ የሚያሳይና ሁላችንም የምንስማማበት እውነት ነው። ሴቶች የጥንካሬ፣ የማሸነፍና የቁርጠኝነት ተምሳሌት በመሆን በህብረተሰቡ ዘንድ አውንታዊ ለውጦችን በማምጣት ላይ ይገኛሉ።

የሴቶች ቀን በአለምአቀፍ ደረጃ በየአመቱ የካቲት 29 የሴቶችን ፖለቲካዊ ፣ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስኬቶችን በማውሳት ይከበራል።
ላለፉት አስርት አመታት የሴቶች ቀን ሴቶችን የምናበረታታበት፤ለሴቶች ያለንን ፍቅርና ክብር የምንገልጽበት መልካም አጋጣሚ ሆኖ ሲያገለግል ቆይቷል።

ዛሬ ሴቶች በአለምአቀፍ ደረጃ በፖለቲካው ዘርፍ፣ በትምህርት ፣ በማህበረሰብ አቀፍ ስራዎች ፣በስፖርት፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በሪሰርች፣ በፈጠራና በተለያዩ መስኮች የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የራሳቸውን አሻራ በማስቀመጥ ላይ ይገኛሉ ።

የሴቶች እኩልነት እንዱ ማሣያ ለሴቶች የሚሠጡ የጤና አገልግሎት ሲሆን ክሊኒካችን ሴት እህቶቻችንና እናቶቻችን ዘመናዊና ጥራቱን የጠበቀ የጤና እንዲያገኙ ይተጋል።

በዚህ አጋጣሚ ይች አለም ያለ ሴቶች ጎደሎ መሆኗን እና ህይወት ከናንተ እንደሚመነጭ እየገለፀኩ እንኳን ለሴቶች ቀን በሰላም አደረሳችሁ ።

መልካም የዓለም የሴቶች ቀን!

ዶ/ር ሎምባሞ ሊራንሶ
ክሊኒካል ዳይሬክተር
ሐዎራ መካከለኛ ክሊኒክ-ሆሳዕና


#march_8 #women #international #WomenHealth

Subscribe to @haworaclinic
Like us on facebook.com/haworaclinic