🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ቫይረስ ከፍተኛውን የሞት ቁጥር አስመዘገበች በኢትዮጵያ የመጀመርያው በኮቪድ | Hawhora Clinic-Hosanna

ኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ቫይረስ ከፍተኛውን የሞት ቁጥር አስመዘገበች

በኢትዮጵያ የመጀመርያው በኮቪድ-19 ቫይረስ የተያዘ ግለሰብ ሪፖርት ከተደረገ ከአንድ ዓመት በኋላ ከፍተኛው የሞት ቁጥር መመዝገቡን የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

ኢንስቲትዩቱ በዕለታዊው መረጃው ይፋ እንዳደረገው በመጋቢት 3 ቀን 2013 ዓ.ም. 27 ግለሰቦች በአንድ ቀን በኮቪድ-19 ቫይረስ ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን፣ እንደዚህ ዓይነት ከፍተኛ የሞት ቁጥር የተመዘገበው ከአስከሬን ላይ ናሙና ተወስዶ በሚመረምርበት ወቅት ነበር።
 በተጠቀሰው ዕለት፣ የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 6,985 ሰዎች፣ ቫይረሱ የተገኘባቸው 1,361 ሲሆኑ፣ 454ቱ ደግሞ በጽኑ ታመዋል፡፡  

በኢትዮጵያ ባጠቃላይ 2,214,180 ተመርምረው፣ ቫይረሱ የተገኘባቸው 172,571፣  ያገገሙ 141,195 ሲሆኑ፣ ባሁን ጊዜ ቫይረሱ ያለባቸው 28,864 ናቸው፡፡ በወረርሽኙ 2,510 ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን አሁናዊው መረጃ ያሳያል፡፡

መዘናጋቱ በዚሁ ከቀጠለ ነገ የእያንዳንዱን ቤት ማንኳኳቱን ሰለማይቀር አሁንም የመከላከያ መንገዶችን  ኅብረተሰቡ በአግባቡ እንዲተገብር የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳስቧል።

አራቱ የ‹‹መ›› ሕጎች
• መራራቅ፡ አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣
• መታጠብ፡ እጅን በተደጋጋሚ በውኃና በሳሙና መታጠብ፣
• መቆየት፡ አስገዳጅ ካልሆነ ቤት ውስጥ መቆየት፣
• መሸፈን፡ ከቤታችን ወጥተን ስንንቀሳቀስ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) መጠቀም፡፡

ምንጭ: ሪፖርተር

@haworaclinic ይቀላቀሉ
#covid