Get Mystery Box with random crypto!

ተደጋጋሚ የፅንስ መጨንገፍ Recurrent pregnancy loss(RPL) ተደጋጋሚ የፅንስ መጨ | Hawhora Clinic-Hosanna

ተደጋጋሚ የፅንስ መጨንገፍ
Recurrent pregnancy loss(RPL)

ተደጋጋሚ የፅንስ መጨንገፍ ምንድነው?

የፅንስ መጨንገፍ አንዲት ነፍሰጡር ሴት እርግዝናው 20 ሳምንት ሳይሞላው በራሱ ጊዜ ሲቋረጥ ነው።

ተደጋጋሚ የፅንስ መጨንገፍ የሕክምና ቃል ሲሆን አንዲት ሴት 3 ወይም ከዚያ በላይ በተከታታይ የጽንስ መጨናገፍ ሲያጋጥማት ነው።

ለተደጋጋሚ የፅንስ መጨንገፍ ምክንያት ምንድነው?

አንዳንድ ሁኔታዎች ለጽንስ መጨናገፍ ምክንያቶች ሊሆኑ ይችላሉ

● የጽንሱ የክሮሞሶም ችግር

ክሮሞሶም በሺዎች የሚቆጠሩ ጂኖችን የያዙ ሴሎች ናቸዉ። የክሮሞሶም ችግሮች አብዛኛውን ጊዜ በአጋጣሚ የሚከሰቱ ናቸው ሆኖም ግን አንዳንድ ጊዜ የሚከሰቱት የእናት ወይም አባት የክሮሞዞም ችግር ስላላቸው ሊሆን ይችላል። ይህ ሁኔታ በአብዛኛው በዕድሜ የገፉ እናቶች ላይ ይከሰታል።

● ከእናትየው የበሽታ መከላከል ስርአት ጋር የተያያዙ ችግሮች

● የእናትየው የውስጥ ደዌ በሽታዎች መኖር። ለምሳሌ የስኳር እና የታይሮይድ በሽታዎች

● የማህጸን የውስጥ ቅርጽ የሚቀይሩ አንዳንድ የተፈጥሮ ወይም ከጊዜ በኋላ የሚከሰቱ ችግሮች

ይሁን እንጂ አብዛኛውን ጊዜ ጊዜ ዶክተሮች የተደጋጋሚ የፅንስ መጨንገፍ ምክንያት ሊያውቁት አይችሉም።

ለፅንስ መጨንገፍ ምክንያት ለማወቅ ሐኪሜ ምን አይነት ምርመራ ያደርጋል?

የፅንስ መጨንገፍ ለምን እንደነበረ ለማወቅ ዶክተርዎ

● ከእርስዎ ጋር እየተነጋገረ ስለ ቀደምት እርግዝናዎ፣ ስለ የወር አበባዎና የጤና ሁኔታዎትን ይጠይቃል

● የማህጸን ምርመራን ጨምሮ አጠቃላይ የአካል ምርመራ ያደርጋል

● የደም ምርመራዎች እንዲያደርጉ ያዝዛል

እነዚህ የሚያጠቃልሉት በሽታ የመከላከያ ስርኣትን፤ የደም መርጋት ስርዓትን እና የሆርሞን ደረጃ ምርመራዎች ነው። በተጨማሪም እንደ ታይሮይድ በሽታ ወይም የስኳር በሽታ የመሳሰሉ አንዳንድ የጤና ሁኔታዎችን ምርመራ ያካትታል።

● አልትራሳውንድ

● ሂስተሮስኮፒ

ይህ ካሜራ ያለው ቀጭን ቱቦ ወደ ማሕፀን ውስጥ አስገብቶ የማህጸን የውስጥ ክፍል ምርመራ ነው።

● የክሮሞዞም ምርመራ

ይህ በዘረ-መል (genetic) ላይ ችግር ካለ ለማወቅ የሚደረግ ምርመራነው።የእርስዎ እና የባለቤትዎ የክሮሞዞም ምርመራ ከመደረጉ በፊት ከጂን ምርመራ አማካሪ ጋር እንዲወያዩ ይደረጋል።

የተደጋጋሚ የፅንስ መጨናገፍ ህክምናው ምንድን ነው ?

ህክምናው መንስኤውን መሰረት ያደረገ ነው። ለምሳሌ

● አንዳንድ ጊዜ በማህፀን ውስጥ ያለን ችግር በቀዶ ሕክምና ሊታከም ይችላል።

● አንዳንድ የበሽታ መከላከያ ወይም የሆርሞን ችግሮች በመድሃኒት ሊታከሙ ይችላሉ።

ድጋሚ የፅንስ መጨንገፍ እንዳይኖር በራሴ የማደርገው ነገር አለ?

የፅንስ መጨንገፍ በእርግጠኝነት እንዳይኖር ለማድረግ የሚያስችል መንገድ የለም። ይሁን እንጂ

● ሲጋራ ፣ የአልኮል መጠጥ፣ ኮኬይንና የመሳሰሉትን ነገሮችን በማቆም እና ክብደትዎን በመቆጣጠር የጽንስ መጨንገፍ እድሎዎን ሊቀንሱ ይችላሉ።

● ለመጸነስ ሲያስቡ ወይም መጸነስዎ እንዳወቁ ወድያውኑ ሃኪም ያማክሩ

ከተደጋጋሚ የጽንስ መጨናገፍ በኋላ መጨነቅና ማዘን የተለመደ ነው። አንዳንድ ሴቶች ግን በጭንቀት ይዋጣሉ። የመንፈስ ጭንቀትዎ የከፋ ከሆነ ግን ሀኪም ወይም ነርስ ያማክሩ።አንዳንድ ሕክምናዎችና የመቋቋሚያ ስልቶች አሉ። አንዳንድ ጊዜም ተመሳሳይ ችግር ካጋጠማቸው ሰዎች ጋር ተገናኝቶ መወያየት ጠቃሚ ሊሆን ይችላል ።

በክሊኒካችን የማህፀንና ፅንስ ህክምና ከተሟላ ምርመራ ጋር በማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ሐኪም በ ዶ/ር ሎምባሞ ሊራንሶ በመሰጠት ላይ ይገኛል።

@haworaclinic ይቀላቀሉ።
0911512338/ 0996237110 / 0996237111 ይደውሉ ።