🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ወራሾች ተለይተው እና የውርስ ሀብቱ ድርሻ ታውቆ ነገር ግን ክፍፍል ሳይደረግ የቆየን የውርስ ሀብት | Corporate Lawyer

ወራሾች ተለይተው እና የውርስ ሀብቱ ድርሻ ታውቆ ነገር ግን ክፍፍል ሳይደረግ የቆየን የውርስ ሀብት በማናቸውም ጊዜ መጠየቅ እንደሚችልና በይርጋ የሚታገድ እንዳልሆነ ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1060 እና ተከታዬቹ ድንጋጌዎች መረዳት ይቻላል።
https://t.me/HenokTayeLawoffice
እንዲሁም ከውርስ ሀብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የውርስ ሀብቱን በእጁ አድርጎ በመገልገል ላይ ያለ ተከራካሪ የሆነ ወራሽ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን የውርስ ንብረት በጋራ ይዞ ከቆየ ሰው ላይ የውርስ ድርሻዬን ልወቅ ወይም ይለይልኝ ጥያቄ በይርጋ ይታገዳል የሚባልበት አግባብ የለም።
https://t.me/HenokTayeLawoffice
#የድምፅ ብክለት


የድምፅ ብክለት ክልከላ ባለቤቱ ስራውን የሚፈፅመው በራሱ ንብረት ወይም ቤት ውስጥ ቢሆንም ድርጊቱ ሌላውን ጎረቤት እንዳይረብሽ፣ እንዳያውክ፣ ወይም ችግር እንዳያስከትል በማድረግ መብቱን ይጠቀም ዘንድ ህጉ ያበጀው የባለቤትነት መብት አጠቃቀምን አድማስ የሚወስን ስርዓት መሆኑን ከአንቀፅ 1226 እና ተከታዬቹ ድንጋጌዎች መረዳት ይቻላል።
https://t.me/HenokTayeLawoffice
ይህን ችግር ለማስወገድ የሚቀርበው አቤቱታ ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1149 ስር ከተመለከተው በይዞታ ላይ ሁከት መፍጠር ተግባር የሚለይ ሲሆን አንዴ የተፈጠረ የድምፅ ብክለት እንዲቀጥል የሚደረግበት አግባብ ስለሌለ በይርጋ የሚታገድ አይደለም።
0953758395
Henok Taye/ሄኖክ ታዬ
በማንኛውም ፍ/ቤት ጠበቃና የሕግ አማካሪ
ለበለጠ መረጃ በቴሌግራም ያግኙ


#HenokTayeLawOffice
#Ethiopia
#AddisAbaba
https://t.me/HenokTayelawoffice