🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የእሽሙር ማህበር በንግድ መዝገብ ላይ እንዲመዘገብ አይገደድም ሲባል???? (by Mengistu Z | Corporate Lawyer

የእሽሙር ማህበር በንግድ መዝገብ ላይ እንዲመዘገብ አይገደድም ሲባል????

(by Mengistu Zegeye)

የእሽሙር ማህበር በተሻሻለው የንግድ አዋጅ መሠረት እንደ ድሮው ሁሉ በንግድ መዝገብ ላይ እንዲመዘገብ አይገደድም። ይህ ማለት ግን ፤የእሽሙር ውል ስምምነቱን በውልና ማስረጃ አይመዘገብም ማለት አይደለም።ማህበርተኞቹ የjoint venture/በጋራ የመስራት ውል ስምምነቱን/በውልና ማስረጃ የማስመዝገብ ምርጫቸው በእጃቸው ነው ።ነገር ግን እንደሌሎቹ ማህበራት የመመስረቻ ጽሁፍ፤የመተዳደሪያ ደንብ፤ቃለ ጉባኤ አያስፈልግም።

ይልቁንስ በኢትዮጲያ የታክስ ህግ joint venture ታክስ የመክፈል ግዴታ ስለተጣለበት የjoint venture ማህበር በታክስ ከፋይነት የመመዝገብ ግዴታ አለበት። /የንግድ ሚኒስቴር የታክስ ምዝገባና ስረዛ መመሪያ ቁጥር 3/2011 እና ቀድሞ በ2001 አም በገቢዎችና ጉምሩክ ወጥቶ የነበረው መመሪያ ቁጥር 11/2001 (ከላይ በተጠቀሰው መመሪያ ቁጥር 3/2001 የተሻረ ነው/ ይመልከቱ/

ስለሆነም ማህበርተኞቹ /ተዋዋዮቹ የእሽሙር ማህበሩን ለታክስ ከፋይነት የማስመዝገብ አስገዳጅ ግዴታ አለባቸው። አለበለዚያ ሰዎች እንደ ማህበር በጋራ በሚያገኙት ገቢ እና በግላዊ የትርፍ ክፍፍል ገቢ ላይ ታክስ ሳይከፍሉ ወደቤታቸው ሊሄዱ የሚችሉበት የነጻ ምሳ/free lunch/ venture የለም። በjoint venture የተደራጁ ሰዎች ማህበራቸው በንግድ ቢሮ መዝገብ ያልሰፈረ ቢሆንም የንግድ ስራ ሰርቶ በሚያገኘው ገቢ ላይም ሆነ ተዋዋዩቹ በሚያገኙት የትርፍ ገቢ ላይ ታክስ የማይከፍሉ ከሆነና ግለሰቦች ይኸው የእሽሙር ማህበር እንዳላቸው ማረጋገጫ የሰጡበት ጠቋሚና አስረጅ ሰነድ ከተገኘ /ለምሳሌ በባልና ሚስት የፍቺ ክርክር ላይ ግለሰቦች/በተለይ የተጋቢ ዘመዶች/ ያንደኛውን ተጋቢ ድርሻ ለመንጠቅ በማሰብ በጋብቻ ዘመን ባልና ሚስቱ ያፈሩትን ንብረት አንደኛው ተጋቢ በስሙ የተመዘገበ ቢሆንም ይኸው ንብረት የእሽሙር ማህበር ንብረት እንጅ የባልና ሚስቱ ስ የጋራ ንብረታቸው አይደለም በማለት ቅንነት የጎደለው ክርክር ላይ ይህን መሠሉ ጥቆማ ሲቀርብ እነዚህ የእሽሙር ማህበር መሥርተን ንብረት የጋራችን ነው የሚሉ ግለሰቦች እስከዛሬ ማህበራቸውን/የእውነት ከሆነ/ ከታክስ ክፍያ ሰውረው ለመንግስት መክፈል የሚገባቸውን የማህበር ገቢ ታክስና የትርፍ ክፍፍል ገቢ ታክስ የመክፈል ግዴታቸውን ባለመወጣት የቆዩ ለመሆኑ ትልቅ ማስረጃ ስለሚሆን ይህንን ገቢያቸውን ለረጅም ጊዜ ደብቀው ሳይከፍሉ የቆዩ ከሆነ ደግሞ በtax evasion እና ታክስ ማጭበርበር ድርጊት የወንጀልና የፍትሃ ብሄር ክስ ሊቀርብባቸው ግድ ይላል ማለት ነው። አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል ነው ነገሩ። እናንተስ ምን ትላላችሁ??