Get Mystery Box with random crypto!

በፍትሐብሄር ክርክር #የሰነድ_ማስረጃ ማቅረብ የሚቻለው መቼ ነው በአብዛኛው ፍ/ቤቶች የጽሑፍ ማ | Corporate Lawyer

በፍትሐብሄር ክርክር #የሰነድ_ማስረጃ ማቅረብ የሚቻለው መቼ ነው

በአብዛኛው ፍ/ቤቶች የጽሑፍ ማስረጃዎች ከክስ ጋር ወይንም ከመከላካያ መልስ ጋር አብሮ ካልቀረበ መቅረብ አይችልም በሚል ሲከለክሉ ይታያል፡፡ ነገር ግን በሥነ-ሥርዓት ህጋችን ግን ከክስ ማመልከቻ ወይም ከመከላካያ መልስ በኋለ ክስ ከመሰማቱ በፊት ከመዝገቡ ጋር ተያይዞ ያልቀረበ የጽሑፍ ማስጃዎች ካሉ መቅረብ እንደሚችሉ ይደነግጋል፡፡

# ሀ . የፅሑፍ ማስረጃዎች በሙሉ ክርክሩን መስማትና ምስክሮችን መመርመር ከመጀመሩ በፊት ተጠቃለው መግባት አለባቸው፡፡

# ለ . በመጀመሪያ ደረጃ ከሳሹ ከክስ ማመልከቻው ጋር ተከሳሹ ደግሞ ከመከላከያ መልሱ ጋር ይጠቅመናል የሚሉትንና በእጃቸው የሚገኙትን ወይም ሊያቀርቡ የሚችሉትን የጽሑፍ ማስረጃ በሙሉ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው (ቁ.223(1)) (ለ) እና 234 (1)፡፡

# ሐ . በሁለተኛ ደረጃ ተከራካሪ ወገኖች ለማቅረብ የሚችሉትንና ይጠቅማናል የሚሉትን ወይም ፍርድ ቤቱ እንዲቀርብ የጠየቀውንና አስቀድመው ፍርድ ቤት ያላቀረቡትን የፅሑፍ ማስረጃ ሁሉ በመጀመሪያው ቀነ ቀጠሮ ማቅረብ አለባቸው
(ቁ. 137 (1)) ፡፡

# መ. ማንኛውም አቤት ባይ ሰነዶችን ከአቤቱታው ጋር በማያያዝ ወይም ከቀነ ቀጠሮው በፊት ወይም በመጀመሪያው ቀነ ቀጠሮ ካላቀረበ በቀር ማስረጃዬ ከፍርድ ቤቱ መዝገብ ጋር ይያያዝልኝ ወይም ለማቅረብ ይፈቀድልኝ በማለት ለማመልከት አይችልም (137(3)፡፡

# ሠ . መቅረብ የሚገባቸው ማስረጃዎች ከተከራካሪዎች ወገኖች ባንዳኛው
ጉድለት ወይም በቂ ባልሆነ ምክንያት ሳይቀርቡ የቀሩ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ወዲያው ፍርድ ይሰጣል (ቁ. 256(1))፡፡

# ረ . ከላይ በ “መ” እና “ሠ” ሥር የተጠቀሱት አጠቃላይ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ከአቤቱታ ጋር ወይም በመጀመሪያ ቀነ ቀጠሮ ያልቀረበ የፅሁፍ
ማስረጃ በሌላ ጊዜ ሊቀርብ የሚችልበት ልዩ ሁኔታዎች (exceptions) አሉ፡፡

እነዚህም፡-
#1. ፍርድ ቤቱ በራሱ አስተያየት ወይም በተከራካሪዎች ወገኖች አመልካችነት
በሌላ ፍ/ቤት ዘንድ የሚገኝ መዝገብ ወይም የጽሑፍ ማስረጃ እንዲቀርብ ማዘዝ
ይችላል (ቁ.148 (11))፡፡

#2. ማስረጃዎቹ ሳይቀርቡ የቀሩት ከባድና በቂ በሆነ ምክንያት መሆኑን ፍርድ ቤቱ ከተረዳ ስለ ክርክሩ አወሳሰንና ማስረጃ ያለመቅረቡ ስላስከተለው ኪሳራ
ተገቢ መስሎ የታየውን ትፅዛዝ በመስጠት ነገሩ የሚሰማበትን ቀነ ቀጠሮ ይወስናል (ቁ. 256 (1)፡፡ (ማስረጃው እንዲቀርብ ማዘዝ ይችላል፡፡)

#3. አስፈላጊ መስሎ ከታየው ፍርድ ቤቱ የክርክሩን ጭብጥ ከመያዙ በፊት በተከራካሪዎች ያልቀረበን የፅሑፍ ማስረጃ በትዕዛዝ አስቀርቦ መመርመር
ይችላል (ቁ. 149 (1) )፡፡

#4. ክርክሩ በሚሰማበት በማናቸውም ግዜ ፍርድ ቤቱ በተከራካሪዎቹ ያልቀረበ
ነገር ግን ለክርክሩ ጠቃሚ የሆነ የፅሑፍ ማስረጃ እንዲቀርብ ለማዘዝ ይችላል
(ቁ.164)፡፡

#5. ምስክሮችን መስቀለኛ ጥያቄ ለመጠየቅ ወይም ምስክሩ ነገሩን ለማስታወስ እንዲችል የሚቀርብ የጽሑፍ ማስረጃ በመጀመሪያ በይቀርብም ክርክሩ በሚስማበት ጊዜ መቅረብ ይችላል (137 (4)) ፡፡
@Henoktayelawoffice

share