Get Mystery Box with random crypto!

የማያሸልሙ 7 የሩጫ ዓይነቶች ከክፍል አምስት የቀጠለ..... | ወንጌል ይለዉጣል📖


የማያሸልሙ 7 የሩጫ ዓይነቶች

ከክፍል አምስት የቀጠለ.....
፨፨በሐጌ 1:5፤7)ላይ
"ልባችሁን በመንገዳቹ ላይ አድርጉ"የሚል ቃል አለ ይሄ ቃል ላነሳውት የክፍል አምስት ርዕስ ከፍተኛውን የማብራራት ሚና የመጫወት አቅም አለው
በሐጌ ዘመን የነበሩ ሰዎች የእግዚሀብሔርን ቤት መስራት ችላ ብለው የራሳቸውን ቤት በትጋት በመስራት ተጠምደው ነበር።
፨፨ጊዜው የእግዚሀብሔርን ሳይሆን የእኛን ስራ የምንሰራበት ነው በሚል እኩይ አስተሳሰብ ተቀንብረው ይነዋልሉ ነበር ከዚህ የተነሳ እግዚሀብሔር በነብዩ በሐጌ በኩል ህዝቤ ከመንገዱ ላይ ልቡን አንስቶ ትላንት በመልካም ያስጀመርኩትን ሠናይ ሩጫ እንደአጀማመሩ በልቡ መሮጥ ትቶ በእግሩ በመሮጥ ላይ ይገኛል እናም በዚሁ ከቀጠሉ መጨረሻቸው ስለማያምር አሁኑኑ ልባቸውን በመንገዳቸው ላይ እንዲያደርጉና በልባቸውም መሮጥ እንዲጀምሩ አሳስብልኝ በማለት አጣዳፊ መልዕክትን እንዲያስተላልፍ ይቀሰቅሰዋል
የሚገርመው እነዚህ ተደራሲያን በልባቸው ባለመሮጣቸው ምክንያት የሚሰሩት ሁሉ በኪሳራ ምች ተመቶባቸው ነበር
ይበላሉ አይጠግቡም
ይጠጣሉ አይረኩም
ይለብሳሉ አይሞቃቸውም
ደሞዛቸውን ይቀበላሉ በቀዳዳ ኪስ ይጨምራሉ
ይዘራሉ ምድር አትተባበራቸውም ነበር የዚህ ሁሉ ምክንያቱ ደግሞ በልባቸው ሳይሆን በእግራቸው በመሮጣቸው ነው
በልባችን በመሮጥ የእግዚሀብሔር ቤት እንስራ
፨፨ልባችንን በመንገዳችን ላይ እናድርግ
፨፨በእግራችን ሳይሆን በልባችን እንሩጥ እላለው
ክፍል 6 ይቀጥላል
እወዳችዋለው
by biruk mohammed