Get Mystery Box with random crypto!

የማያሸልሙ 7 የሩጫ ዓይነቶች ክፍል ስድስት | ወንጌል ይለዉጣል📖


የማያሸልሙ 7 የሩጫ ዓይነቶች

ክፍል ስድስት

፨ወንድምን ጠልፎ መሮጥ
አያሸልምም
ተወዳጆቼ ከዚህ በፊት አምስቱን የማያሸልሙ የሩጫ ዓይነቶች ለመዳሰስ ሞክረናል ለማስታወስ ያህልም፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ግብን እያዩ አለመሮጥ
አያሸልምም
የሩጫውን መርህ ሳያከብሩ
መሮጥ አያሸልምም
ሩጫውን አቋርጦ መውጣት
አያሸልምም
በበቂ ዝግጅት ያልታገዘ ሩጫ
አያሸልምም
በልብ አለመሮጥ አያሸልምም
ዛሬ ደግሞ ስድስተኛውን የማያሸልም የሩጫ ዓይነት በጥቂቱ ለመዳሰስ እንሞክራለን
"""ወንድምን ጠልፎ መሮጥ
አያሸልምም""
፨የሚገርመው ወንድምን ጠልፎ በመጣል ቀዳሚ ሆኖ መገኘት አለብኝ የሚልን እኩይ ቢሂል አንግተው የሚንቀሳቀሱ ሰዎች በተለይ በዚህ ዘመን እንደ አሸዋ ለመቁጠር እስኪያዳግት ድረስ በዝተዋል።
እነዚህ ሰዎች ከወንድማቸው መዘግየት ውስጥ
ፍጥነታቸውን ለማምረት የሚፈልጉ፥
ከወንድማቸው ሀዘን ውስጥ ደስታን ናፋቂዎች እና
በተጨማሪም ደግሞ፦፦፦፦፦፦፦፦
ከወንድማቸው ኪሳራ ውስጥ ትርፋቸውን ለመገብየት በማሰብ ዘምቢል ይዘው የሚንቀሳቀሱ ሰዎች ናቸው።
ተወዳጆቼ ሆይ እናስተውል ወንድማችንን ጠልፎ በመሮጥ የምናገኘው የትኛውም ሽልማት እንደ እግዚሀብሔር ቃል ከተመለከትነው ልክ እንደ መርዘኛው እንቦጭ ነው። ለዓይናችን ልምላሜ መስሎ እየታየን ቀስ በቀስ ግን ሁለንተናችንን እየገደለ የሚጓዝ በቀላሉ ተዛማች የሆነ ገዳይ መርዝ ነው።
(((((ፊል 2:3-4))))))
በዚህ ክፍል ላይ ከባልንጀሮቻችን ጋር በትህትና አቆጣጠር መሮጥ እንደሚገባን ይነግረናል
፨ሶስት ነገሮችን በትህትና እየቆጠርን አብረናቸው እንሩጥ ይለናል
1)ባልንጀራዬ ከእኔ እንደሚሻል
መቁጠር
2)ለባልንጀራዬ የሚጠቅመውን ነገር ሁሉ ልክ እንደ እኔ ማግኘት እንደሚገባው በአስተሳሰብ መቁጠርና
3)በከንቱ ውዳሴን ለማግኘት አስቦ አንዳች ነገር አለማድረግን በመቁጠር እንድንሮጥ ያበረታታናል።ከዚሁ ጋር አያይዘንም ትህትናን ከዚህ ክፍል ዐውድ አንፃር እንደዚህ መረዳት እንችላለን።
ተባብረን ተጋግዘን እንሩጥ
የመጨረሻውን ክፍል እባኮዎን በትዕግስት መስመር ላይ
ይጠብቁኝ
እወዳችዋለው
by biruk mohammed