Get Mystery Box with random crypto!

የማያሸልሙ 7 የሩጫ ዓይነቶች የመጨረሻው ክፍል ሰባት | ወንጌል ይለዉጣል📖


የማያሸልሙ 7 የሩጫ ዓይነቶች

የመጨረሻው ክፍል ሰባት

እጅግ በጣም የምወዳችሁ የአባቴ ብሩካኖች በቅድሚያ ሰላምታዬ ይድረሳቹ እያልኩኝ በመቀጠል ደግሞ የመጨረሻውን ክፍል ወደ ማካፈሉ መንደር እዘልቃለው።
"በፍቅር አለመሮጥ
አያሸልምም"
ስለ ፍቅር ጉዳይ ሲነሳ አለማችን ብዙ ዓይነት መረዳቶችን አንግታ እንደምትንቀሳቀስ ይታወቃል።ከሁሉም በላይ ግን መፅሀፍ ቅዱሳችን ፍቅርን በተመለከተ የሚሰጠን መረጃ በትልቁ ውሀ የሚያነሳ ነው።

ፍቅርን ከመፅሀፍ ቅዱስ አንፃር ከማየታችን በፊት በግሪኩ በስንት እንደሚከፈል እንመልከት፦፦፦፦፦
ፍቅር በግሪኩ በ8 ይከፈላል
1)ፊልያ፦የወንድማማች ፍቅር
2)ኢሮስ፦የእጮኝነት ፍቅር
3)ስቶርጅ፦የቤተሰብ ፍቅር
4)ሉዳስ፦ለአካለ መጠን ባልደረሱ ወንድና ሴት መሀል የሚፈጠር ፍቅር
5)ፕራግማ፦በባልና በሚስት መሀል ብቻ ያለ ፍቅር
6)ፊላሺያ፦ራስን መውደድ(አዎንታዊና አሉታዊ ገፅታ ያለው ነው
7)ፓትሮቲዝም፦የሀገር ፍቅር
8)አጋፔ፦የእግዚሀብሔር ፍቅር
ከእነዚህ የፍቅር አይነቶች መካከል እኛ አማኞች እንዲሁ የተካፈልነው የእግዚሀብሔርን ፍቅር ነው
የተካፈልነው የእግዚሀብሔር ፍቅር ቢያንስ ቢያንስ ሶስት ነገሮች ላይ የተመሰረተ ነው፦፦፦፦፦፦፦
A)በጥልቅ መስዕዋትነት ላይ
B)እንካ በእንካ ባልሆነ መሠረት ላይ እና
C)ከፍርድ ይልቅ ወደ ምህረት በኩል ባዘነበለ መሠረት ላይ የተመሰረተ ፍቅር ነው።
ይቀጥላል.............................
አደራ በትዕግስት ጠብቁኝ
እወዳችኋለው
by biruk mohammed