Get Mystery Box with random crypto!

የማያሸልሙ 7 የሩጫ ዓይነቶች ከክፍል ሰባት የቀጠለ........ ስለ ፍቅር | ወንጌል ይለዉጣል📖


የማያሸልሙ 7 የሩጫ ዓይነቶች

ከክፍል ሰባት የቀጠለ........
ስለ ፍቅር ሲነሳ ብዙ ነገሮችን መዳሰስ ይቻላል ነገር ግን ከዚህ ትምህርት አንፃር የመጨረሻውን ሀሳቤን እንካዋቹ ልበልና ሀሳቤን በመልካም ላሳርገው፦፦፦፦፦፦፦
በክርስትናው አለም ውስጥ በትራኩ ላይ ስለሮጥን ብቻ ተሸላሚዎች እንሆናለን ማለት አይደለም።ሩጫው በፍቅር መሮጥን ይጠይቃል።ብዙዎቻችን መሮጣችን ላይ እንጂ በፍቅር መሮጣችን ላይ ብዙ ጊዜ ትኩረት ስናደርግ አንታይም።
ፍቅር የህግ ሁሉ አራት ነጥብ እንደሆነ ቅዱስ ቃሉ በተለመደው ትህትናዊ ቃላቱ በተለያዩ ስፍራዎች ላይ አስፍሮልን ይገኛል።ለምሳሌ(ማቴ 22:36-40)
ሐዋሪያው ጳውሎስ የፍቅርን ትርጉም በ1ጢሞ 1:5 ላይ የገለፀበት መንገድ በቀላሉ ለመረዳት የሚቀል ሆኖ አጊኝቼዋለው፦፦፦፦፦
ፍቅር በዋናነት ሶስት ነገሮችን በውስጡ እንዳቀፈ ክፍሉ ያሳብቀናል፦፦፦፦፦፦
1)ንፁህ ልብ፦ይሄ ማለት
ከክፋት ያልተዳቀለ ልብ
በሌሎች ስኬት የማይቀና ልብ
የክርስቶስን መስቀል
የሚተነፍስ ልብ ወዘተ..
2)በጎ ህሊና፦በጎ ህሊና ማለት በክፉ መረብ ያጠመደንን ሰው ከወጥመዱ ካመለጥን ማግስት መልሰን ገንዘባችን ለማድረግ የምንወስደው አዎንታዊ እርምጃ ማለት ነው።
3)ግብዝነት የሌለበት እምነት፦፦
ግብዝነት ማለት በማስመሰል ማንነት የተከፈነ ትወናዊ ህይወት ማለት ነው ግብዝነት የሌለበት እምነት ሲል ትወናዊ ያልሆነና በእውነተኛ ማንነት የተገለጠ እምነት ለማለት ፈልጎ ነው
በአጠቃላይ ከዚህ ክፍል አንፃር ፍቅር ማለት
ንፁህ ልብ
በጎ ህሊናና ግብዝነት የሌለበት እምነት
ማለት ነው።
ተወዳጆቼ ሆይ ቀሪውን ዘመናችንን በፍቅር በመሮጥ ለታላቁ ሽልማት በክብር እንድረስ እላለው።
እወዳችኋለው
by biruk mohammed