Get Mystery Box with random crypto!

አለመደሰት አልችልም። እውነተኛ ደስታ ከውስጥ ወደ ውጭ የሚፈስ ነው፡፡ ከመንፈሳችን ይነሳና ነፍሳች | ወንጌል ይለዉጣል📖

አለመደሰት አልችልም።
እውነተኛ ደስታ ከውስጥ ወደ ውጭ የሚፈስ ነው፡፡ ከመንፈሳችን ይነሳና ነፍሳችንን
አጥለቅልቆ ወደ ውጭ ይወጣል( ፊታችን የፈካ እንዲሆን ያደርጋል)::
የእውነተኛ ደስታ መነሻ ስፍራው አካባቢ አይደለም፡፡
ብዙ ሰዎች ይጠይቁኛል፤ "አስቸጋሪ ሁኔታዎችና ማይመች አካባቢ ውስጥ ሆነህ እንኳ
ምትደሰትበት ሚስጥሩ ምንድነው?" ይሉኛል፡፡ መልሴ፡ "የደስታዬ ምንጭ( source)
አካባቢዬና ሁኔታዎቼ አይደሉም" የሚል ነው፡፡
ጳውሎስ፡ የፊልጵስዩስ ክርስቲያኖችን "# ሁልጊዜ # በጌታ ደስ ይበላችሁ" ነው ያለው፡፡
የሚገርመው፡ ጳውሎስ ይሄን መልዕክት የተናገረው እስር ቤት ውስጥ ሆኖ ነው፡፡ ሰው፡
እስር ቤት ውስጥ ሆኖ እንዴት "#ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ" ሊል ይችላል?
...አዎን፡ ይቻላል!
እውነተኛ ደስታ ከውስጥ-ወደውጭ( Inside-out) ነው
የእኔ ደስታ የተመሰረተው ከውስጥ ወደ ውጭ እንጂ ከውጭ ወደ ውስጥ አይደለም። በአመት 365 ቀን 12 ወር 8760 ሰአት 525600 ደቅቃ 31536000 ሰከንድ 892160000 ማይክሮ ሰከንድ ደስተኛ ብቻ ነኝ አለመደሰት አልችልም ።