Get Mystery Box with random crypto!

ኤፌሶን ምዕራፍ 1 [[1 በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ፥ በኤፌሶን | ወንጌል ይለዉጣል📖

ኤፌሶን ምዕራፍ 1

[[1 በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ፥ በኤፌሶን ላሉት ቅዱሳን በክርስቶስ ኢየሱስም ላሉት ምእመናን፤]]

be ቁ 1lay ሐዋርያው በማን ፈቃድ የማን ሐዋርያ እንደሆነ ይናገራል ጳውሎስ እንደ ሌሎቹ ሐዋርያት ሹመቱን ከሌሎች እጅ አልተቀበለም ወንጌልንም ከሰዎች አልተሰበከም ሐዋ9 lay ክርስቶስ ተገልጦለት ነው ወደዚህ ጥሪ የገባው ይህም አስቦበት ሳይሆን የእግዚአብሔር እቅድና ፈቃድ ነበር ምክንያቱም እሱ የአሕዛብ ሐዋርያና ፀረ ክርስቲያን ወሪ የነበረ ሰው ነበር ነገር ግን የእ/ር ፈቃድ የክርስቶስ ሐዋርያነት ስለነበር ተቀይሯል ምንም ያህል አሳዳጅ ቢሆንም ከእ/ር እቅድ ማምለጥ አይቻልም ፥ <<የኢየሱስ ክርስቶስ>> በማለቱም የክርስቶስ ሰራተኛ መሆኑን ያሳያል

ሌላው የሚፅፍላቸውን ሰዎች <<ቅዱሳን>> ይላቸዋል እኚ ሰዎች የመጀመሪያ ታሪካቸው ሲታይ አሕዛብ የነበሩና ጣኦት የሚያመልኩ ሰዎች ነበሩ በዛም ብዙ የዝሙት ስራ ይደረግ ነበር በከባድ ተፅእኖ ውስጥ የነበሩና ከዛም በስተጀርባ ክፉ ኃይላት እንደነበሩ መፀሐፍ ይናገራል (1፥19-20 ፤ 2፥1-2 ፤ 3፥10 & 6፥11-12)
ታዲያ እነዚህ ሰዎች ቅዱሳን የሆኑት እንዴት ነው ስንል ቀደም ሲል የስጋቸውን እና የልቦናቸውን ፈቃድ የሚያደርጉ የነበሩ በበደላቸው የሞት ፍርድ የተገባቸው ነበሩ ነገር ግን በክርስቶስ በማመን የእግዚአብሔርን ምህረት የተቀበሉ ከስጋም ስራ ያመለጡ ሆነዋል ፤ በቀደመው ሥርዓት ቅዱስ የሚለው ስም ለሰዎች የሚሰጣቸው በሃይማኖት ተቋማት ሲሆን ቃሉም የሚፈታው <<ቅዱስ በሆነ ሕይወት ይፋዊ እውቅና ያገኘ>> በሚለው ሃሳብ ነበር ፡ የሞተ ሰውም እንደዛ ለመባል ያሰው በባህሪው እና በአኗኗሩ ነቀፋ የሌለበት ቢያንስ 2ተአምራትን ያደረገ መሆን ነበረበት ።

ታዲያ እነዚህ ሰዎች ቅዱሳን የሆኑት እንዴት ነው ካልን በባሕሪም ይሁን በአኗኗር (ሐዋ 19) ፈፅሞ ተቃራኒዎች የነበሩ ቢሆንም ግን የቀደመው ህይወታቸዉ አሁን ላለው ህይወታቸዉ ምስክር ሊሆን አይችልም ምክንያቱም የተለያየ ዓለም ዉስጥ ነበሩ ያኛው አለም የኃጢኃት ዓለም ሲሆን ይሄኛዉ ደግሞ የፅድቅ ዓለም ነው <<ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው አሮጌው ሁሉ አልፏል>> ያረጀ እና የተናቀ ያለፈ ሕይወታቸው ነበር ያኛው ዛሬ ላይ በክርስቶስ ስራ በማመን ቅዱሳን ሆነዋል
ላለፈው ሕይወት የሞቱና በአዲስ ሕይወት የተነሱ ሆነዋል ቅዱስ ለመባልም ነውር በሌለው የህይወት ኃይል ተነስተዋል ስለዚህ ኩነኔ የለባቸውም ፤

ሌላው <<በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት>> የሚለው ቃል እነዚህ ሰዎች አሁን ላይ በዓለም ስርዓት የሚኖሩ ሳይሆኑ በክርስቶስ የሕይወት ዓለም ውስጥ መሆናቸውን እና በክርስቶስ ማመናቸዉን ያስረዳል <<ቅዱስ>> <<የተለየ>>።

<<ምእመናን>> ወይም ሌላ ትርጉሙ <<የታመኑ>> በክርስቶስ ኢየሱስ ያሉትን የሚያመለክት ነው ሰዎቹ የዳኑት ታማኞች ስለሆኑ ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ስላመኑ እና ስለዳኑ ነው።

[[2 ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።]]

ከአባታችን እ/ር ከጌታም ኢየሱስ <<ፀጋ>> የግሪክ ሰላምታ <<ሰላም>> የአይሁድ ሰላምታ ነው፤
በኤፌሶን መፀሐፍ ጳውሎስ 12 ጊዜ ፀጋ የሚል ቃል ጠቅሷል <<ፀጋ>> <<ለማይገባቸው ሰዎች እግዚአብሔር ያሳየውን ቸርነት>> ያሳያል

<<ሰላም>> ከእ/ር የሚገኝ የመንፈስ እረፍትና መረጋጋት ነው።

ቁ፫ <በረከት> ይቀጥላል