Get Mystery Box with random crypto!

እንግዲህ ጳውሎስ በዚህ መፀሐፍ ውረሱ እያለን ነው ኤፌ3፥8 ኤፌሶን 1፥3 [[[3 በክርስቶስ በ | ወንጌል ይለዉጣል📖

እንግዲህ ጳውሎስ በዚህ መፀሐፍ <<ፍለጋ የሌለውን የክርስቶስን ባለ ጠግነት>> ውረሱ እያለን ነው ኤፌ3፥8

ኤፌሶን 1፥3
[[[3 በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።]]]

ስለዚህ ባለጠግነት ከማውራታችን በፊት ስለ በረከቱ ምንነት ማወቅ ያስፈልጋል

ይህ ባለጠግነት እንደዘመኑ የብልፅግና ሰባኪያን ምድር ምድሩን የሚያስናፍቅ ገንዘብ ገንዘብ ሚሸት አይደለም ክብር ዝና ሀብት አያስናፍቅም

አንዳንድ ሰዎች መንፈሳዊነት የሚመስል ምኞት አላቸው አትመኝ የሚለውን ቀይረውት <<ሀይልን በሚሰጠኝ>> በሚመስል ጥቅሳዊ ምኞት ውስጥ ተጠምደዋል ይሄ ኃጢአት ነው ምክንያቱም ጥረን ግረን እንድንበላ እና እንድናገኝ ታዘናል <<ሊሰራ የማይወድ አይብላ>> ነው ቃሉ 2 ተሰ 3፥8-10

እዚህ ጋር ዋናው መርሳት የሌለብን ነገር እግዚአብሔር የእጃችንን የጉልበታችንን ፍሬ እንደሚባርክ ነው የሰማዮ አባታችን በረከት አያልቅበትም ምክንያቱም እርሱ ባለጠጋ ነው እየሰጠ ይሞላለታል ስለዚህ በምድርም መቶ እጥር እናፈራለን ማለት ነው በበረከቱ ይባርከናል


ነገር ግን ጳውሎስ በዚህ መልእክት ሊነግረን የፈለገው ስለዚህ በረከት ሳይሆን ስለ <<መንፈሳዊ በረከት>> ነው። በዚህ ውስጥ

1 በማን
2 የት
3 በምን ያህል
4 ማን የሚሉትን ሃሳብ እናያለን
5ምስጋና

((1)) በማን <<በክርስቶስ>> በማለቱ ይህ በረከት በክርስቶስ በኩል የሚገኝ መሆኑን ያስረዳል ፡ አማኝ በክርስቶስ ያመነ እለት የእግዚአብሔር መንግስት መራሽ ሆኗል በክርስቶስ ያመንን እለት አብ በልጁ አበልፅጎናል

((2)) የት <<በሰማያዊ ስፍራ>> ክርስቲያን ዜግነቱም ሀገሩም ተስፋውም አባቱም ልቡም በሰማይ ነው ለዛም ነው ሀብትን በሰማይ እንድናከማች መ.ቅ ሚነግረን ስለዚህ አምላካችንም በሰማያዊ በረከት በክርስቶስ አበልፅጎናል

((3)) <<በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ>> ሁሉ የሚለው ቃል የሚቀር ነገር እንደሌለ ያሳያል ይህ በረከት መንፈሳዊ ዓለም ውስጥ ያሉትን በረከቶች ሁሉ ይዟል
እዚህ ላይ ገላ 5:22 ላይ ያሉትን የመንፈስ ፍሬዎች እና የፀጋ ስጦታዎች ማንሳት ተገቢ ነው ይነበብ
ዕብ 2፥4 ሮሜ 12፥6-8 1ጴጥ 4፥10-11 1ተሰ 5፥19-22 1ቆሮ 12፥4-11 : 28-31 ፤ 13፥1-3 ፤ 14፥16-40።
ከምንም በላይ እግዚአብሔር በክርስቶስ ድነትን ሰቶናል በመዳናችን ደግሞ የመንፈስ ቅዱስን ማደሪያዎች ሆነናል በመሰረቱ ክርስቲያን የሁለት ዓለም ሰው ነው በምድር እያለ በሰማይም የሚኖር ነው <<ከክርስቶስ ጋር አስቀመጠን>> ስለሚል እስኪ ሰማይ ላይ ያለውን አለም 1min ጨፍነን እናስበው የበጉ ዙፋን፡ አምልኮት፡ አክሊል፡ መላዕክት፡ ቅዱሳን፡ በጉ ብርሃን የሆነበት ክርስቶስን ምናይበት የመንግስተ ሰማይ ዉበትና አኗኗር … እናስበው እስኪ ያልወረስነው ምናለ…

((4)) ማን የሚለውን ስናይ የበረከታችን ምንጭ ምን እንደሆነ ይነግረናል

<<የጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት>> ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍፁም ሰው እና ፍፁም አምላክ ነው በዚህም በፍፁም ሰውነቱ እግዚአብሔር አምላኩ ነው ፡ በፍፁም አምላክነቱ ደግሞ እግዚአብሔር አባቱ ነው ። ስለዚህ የበረከታችን ምንጭ አባታችን ነው ልጅነትንም ያገኘነው በክርስቶስ ነው፡ አንድ አባት ለልጁ ማያወርሰው ነገር የለም ከሚጎዳው ነገር ውጪ ሁሉ ለልጁ ነው እንግዲህ አባታችን ያለውን እንይ

((5)) ምስጋና ሐዋርያው ይባረክ እያለ እግዚአብሔርን ሲያመሰግን እናያለን የማመስገናችንም ምክንያት <<በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ>> ስለመባረካችን ነው።

አንድ ጠቅላይ ሚኒስተር ወንበሩ ላይ ተቀምጦ አይኖርም ስራውን ሁሉ ይሰራል ነገር ግን እሱ ከወንበሩ ላይ ስለተነሳ ስልጣኑን አያጣም የትም አገር ቢሄድ ያ ወንበር የሱ እንደሆነ እርግጥ ነው እኛም በምድር ላይ በተለያየ ሁኔታ ልንኖር እንችላለን አንድ ግን እርግጠኛ ምንሆንበት ነገር ከልጅነት ስልጣናችን ማንም እንደማይነቀንቀን ነው ምድር ላይ እያለን ሰማይ ላይ ስላለው ሕይወታችንና ቦታችን እርግጠኞች ነን ምክንያቱም ከአባታችን የበረከት ባለጠግነት ሁሉ ተካፋዩች ስለሆንን ስለዚህ ስለ መንፈሳዊ በረከቶች ስለ መንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ሁሉ አመስጋኞች መሆን አለብን አመስጋኝ ብቻ ሳይሆን እንደ ደሀ ሳይሆን እንደ ባለጠጋም አኖር አለብን እርሱን በይቀን ማንቀበለው አለቀብኝ ምንባለው ነገር የለም ምንድነው የነፍሳችን መሻት መዘመር ነው እሱን እንጠይቅ መስበክ ነው መፀለይ ነው ትንቢት ነው አጋንንት ማስወጣት ነው… በምድርስ ምንድነው ሰርተን ያልሆነልን የሁሉም ጥያቄ መልስ አንድ ነው አምላክና አባት የሆነውን እግዚአብሔርን በክርስቶስ መጠየቅ የዛኔ ከባለጠግነቱ ያጠግበናል God bless You እንግዲህ እንደ ባለጠጋ እንኑር