🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

………… .............በአንድ ውብ ቀን የሃሳብ ጅረት አዕምሮዬን ሲወጥረው የከተማዋን ጠር | ቅኔ ያለው ትውልድ

…………

.............በአንድ ውብ ቀን የሃሳብ ጅረት አዕምሮዬን ሲወጥረው የከተማዋን ጠርዝ ይዤ ፍርስራሹ ብቻ በቀረ አንድ የተዘነጋ ቤት በራፍ አለፍኩ፡፡

በፍርስራሹ ውስጥ አንድ ውሻ በቆሻሻውና በአመዱ ላይ ተኝቶ አየሁ፡፡ ቆዳው ቆሳስሏል፣ የተጉዳ አካሉን ህመም ሰቅዞታል። የምትጠልቀውን ፀሃይ ደጋግመው የሚመለከቱት አይኖቹ ሃፍረት፣ ተስፋ መቁረጥና ስቃይ ይነበብባቸዋል፡፡

የእንስሶችን ቋንቋ ባውቅና ሃዘኔን ልገልፅለት ብችል ብዪ እየተመኘሁ በቀስታ ተጠጋሁት። ወደ እሱ መቅረቤ ግን አስፈራውና በተልፈሰፈሱ እግሮቹ ለመነሳት እንዲሞክር አደረገው፡፡ መልሶ እየወደቀ ቁጣና ልመና በተቀላቀለበት አስተያየት ዞሮ ተመለከተኝ፡፡ አስተያየቱ ከወንድ ንግግር የጠራ፣ ከሴት እንባ የቀደመ ነበር፡፡ እንዲህ ያለኝ
መሰለኝ:

«ሰውዬ ፣ በአንተ ጭካኔ እና ክፋት ሳቢያ ብዙ ስቃይ አይቻለሁ ...

«ጉዳት ከሚያደርስብኝ እግርህ ርቄ እዚህ ከትሜያለሁ፣ አፈርና አመድ ከሰው ልጅ ልብ ይልቅ ቅን ናቸውና፣ እነዚህ ፍርስራሾች ከሰው ነፍስ የላቀ ስቃይ የለባቸውምና፡፡ ሂድልኝ፣ ህግና ፍትህ ከሌለበት ዓለም የመጣህ አንተ ...

«የአዳምን ዘር በእምነት እና በክብር ያገለገልኩ የስቃይ ቋት ፍጥረት ነኝ፡፡ የሰውን ልጅ ጠዋትና ማታ በመጠበቅ ታማኝ ጓደኛው ነበርኩ፡፡ ከአጠገቤ ሲለይ አዝኛለሁ፣ ዳግመኛ ሲመለስ በደስታ ተቀብዬዋለሁ፡፡ ከሰሃኑ በሚረግፈው ፍርፋሪ ጠግቤያለሁ፣ ከጥርሶቹ በሚወድቀው አጥንት ተደስቻለሁ፡፡ ነገር ግን ዕድሜዩ ሲገፋና በታመምኩ ጊዜ ከቤቱ አባርሮ ለምህረት የለሾቹ የመንገድ ልጆች ወረወረኝ

«የአዳም ልጅ ሆይ፣ በእኔ እና ዕድሜ በተጫናቸው ዘመዶችህ መሀል አንድነት ይታየኛል። በአፍላ ዕድሜያቸው ለሃገራቸው ተዋግተው በኋላ ላይ አፈሯን የሚገፉ አሉ፡፡ አሁን ግን የህይወታቸው ክረምት ደርሶ እርባና የለሽ ተብለው ወደ ጎን ተገልለዋል ...

«በእኔ ዕድል እና ልጃገረጅ ሳለች የወጣት ወንዶችን ልብ በምታቀልጥ ሴት መሃልም አንድነት ይታየኛል፡ በኋላ ላይም እናት እንደመሆኗ ህይወቷን በሙሉ ለልጆቿ ትሰዋለች። አሁን ግን እድሜዋ ገፍቶ ተረስታለች፡ ተገፍታለች፡፡
እንዴት ጨካኝ ነህ! የአዳም ልጅ! እንዴት ጨካኝ ነህ!!»

ዲዳው እንስሳ ሊነግረኝ የፈለገውን ልቤ ተረዳችው፡፡
{ኻሊል ጂብራን}


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!