🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ማሰብ ምንድነው? ሰው በማሰቡ ከእንስሳት ይለያል ሲባልስ እንዴት ነው?...የሰው ልጅ ምንን ስላሰበ | ቅኔ ያለው ትውልድ

ማሰብ ምንድነው? ሰው በማሰቡ ከእንስሳት ይለያል ሲባልስ እንዴት ነው?...የሰው ልጅ ምንን ስላሰበ ነው ከእንስሳት የሚነጠለው? ወይስ እያሰበ መሆኑን(ማሰብ መቻሉን ማወቁ) ነው? ከእንስሳት ልዩ የሚያደርገው ። እንስሳት ወደ ማይሆን አቅጣጫ ሲጓዙ እረኛቸው እንደሚያግዳቸው ሁሉ ማሰብ እረኛችን ትሆን? እንዲህ ከሆነ የሰው ልጅ መች እረኛውን ሰማ? ከኔ ጀምሮ ።

ማሰብ ከእንስሳት የተለየንበት ሳይሆን ከአራዊት ይልቅ አውሬነታችን የተገለጠበት ከትንኝም በታች ቅንጣት ያከልንበት ሁኔታ ነው ። ማሰብ ነውራችንን አደባባይ ያሰጣብን ከእኔነታችን ያጣላን ከእንስሳት ዝቅ ያረገን ነገር ነው ።

" ዘሎ ገደል የገባ እንስሳ የትኛው ነው? የሰው ልጅ ብቻ ። መውደቅ አውቆ ማጥፋት አስቦ መጥፋት የሰው ልጅ ብቸኛ መለያ ነው...የማያስብ እንስሳ ጥፋት ከሚያስብ የሰው ልጅ አጥፊነት እናሳ ከሆነ የሚያስብ የሰው ልጅ ጥፋት በማያስብ እንስሳ ካልተደረገ ከሁለቱ አናሳው ማን ነው? ያሰበውስ? የደመ-ነፍስ እውቀት ከነፍሳዊ እውቀት ከተሻለ ሰው ክብሩን ለእንስሳ ሊለቅ ይገባዋል ። በእርሱ የተደረገው ጥፋት በእሪያዎች የለምና..."

አለማሰብ ባይቻልም ማሰብን መመኪያ ለማድረግ የሰው ልጅ እጅግ ብዙ ይቀረዋል ። ይህች ውብ ዓለም እናስባለን በሚሉ አደናቁርቶች ጠፍታለች ። ረሃብ የሰው ልጆች የተንኮል ቀመር ነው ። ጦርነት የሰው ልጆች ያለማሰብ ውጤት ነው በሽታ በሰው ልጆች ተቦክቶ ይጋገራል...የዋሆች ይመገቡታል ፈጥነው ይሞታሉ ። ይህ የሰው ልጅ የማሰብ ውጤት ነው ግን ይህ ዓይነት ጭካኔ በእንስሳት አልተደረገም ። ስለዚህ ከሚያስበው የሰው ልጅ እንስሳቶች በለጡ ። የተበለጠ ጎበዝ የሰው ልጅ ብቻ ነው ። ያሸነፈ ተሸናፊ ።

ማሰብ የመሆን ምክንያት አይደለም ። መሆን ግን አብዛኛውን ግዜ የማሰብ ሳይሆን የመፈለግ ውጤት ናት...አስበን አንፈልግም የፈለግነውን እናስባለን እንጂ ።

" የይሁዳ ድልድይ እና ሌሎች ሃሳቦች " ከገጽ 23-26 የተቀነጨበ


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!