Get Mystery Box with random crypto!

አንቺን እንዲሰጠኝ ሆንኩኝ አምላክ ለማኝ ጧፍ መባ ገዛሁ ልሰጠው ከሰማኝ፡፡ አንቺዬ ፀሎቴን ሳልጨ | ቅኔ ያለው ትውልድ

አንቺን እንዲሰጠኝ ሆንኩኝ አምላክ ለማኝ
ጧፍ መባ ገዛሁ ልሰጠው ከሰማኝ፡፡
አንቺዬ
ፀሎቴን ሳልጨርስ ብትይ እመጣለሁ
እኔ እኮ ሞኝ ነኝ
ፈጣሪዬን ትቼ እጠብቅሻለሁ፡፡
እጠብቅሻለሁ
በተገተርኩበት
እጠብቅሻለሁ
በተፈጠረኩበት፡፡
ጊዜ አይፈራረቅ አይጮኹም አእዋፍ
አንቺን ስጠብቅሽ
ለኮስኩት ጨክኜ ለስለት እንዲሆን የገዛሁት ጧፍ፡፡
ትመጫለሽ አይደል?

(ኤልያስ ሽታኹን)


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!