የፈጣሪ ልሳን እጆቼን ዘርግቼ ....... ልጸልይ ፣ ልማልድ ፣ ከደጅኽ ተገኘኹ ፤ አንጋጥጬ ሽቅብ በሐሳቤ ዋኘኹ ። ተንበርክኬ ለምሕላ በግንባሬ ተደፍቼ ቀና ማለት ተዘነጋኝ ፤ የቃል ጸሎት ረስቼ ። ያንደበትኽ ልሳን ከየት ተሰወረ ? ቃል ከምላሴ ላይ እንደምን ታወረ ? ዝም ........ ! ዝም ዝም ........... ! እንደው ዝም ! ዝምታዬ ቀረ ፤ ሰምተኸኛል አንተ ፤ በዝምታ ልሳን ጸሎቴም ሰመረ ። የሞት ጥቁር ወተት ( ተስፋኹን ከበደ ) ╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀: @keney_serezoch @keney_serezoch ╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ ፍቅር አሁን !! 145 viewsedited 10:24