Get Mystery Box with random crypto!

' #ልጄ ደረሰችልኝ ስል #ሞት_ሊነጥቀኝ ነው #እናት ይህች ምስኪን እህታችን #ነቢያት_ሰኢድ ትባ | ቅኔ ያለው ትውልድ

" #ልጄ ደረሰችልኝ ስል #ሞት_ሊነጥቀኝ ነው #እናት

ይህች ምስኪን እህታችን #ነቢያት_ሰኢድ ትባላለች!!
22ዓመቷ ነው!ደግ አባቷ ከሞተ በኋላ ከሁለት እህቶቿ ጋር አባኮራን ሰፈር ሀብተጊዮርጊስ አካባቢ #እናቷን ለማኖርና ለማስደሰት ደፋ ቀና እያሉ ይኖሩም ነበር!!

የዘንድሮ የአካውንቲንግ ተመራቂዋ ነብያት ከወራት በፊት ማዞርና ድካም ሲሰማት እናት ተደናግጣ ራስ ደስታ ሆስፒታል ስትወስዳት ምንም ደም እንደሌላትና በአስቸኳይ ወደ ጥቁር አንበሳ ለተጨማሪ ምርመራ ይዘሻት ሂጂ ብለው ላኳት!!

እናትና ልጅ በታላቁ የረመዳን ፆም ያላሰቡት መርዶ ያልጠበቁት ዱብዳ ገጠማቸው!!የነቢያት የአጥንት መቅኔ ደም ማምረት አቁሞዋልና ቶሎ ወደ ውጪ ሄዳ መታከም አለባት ተባሉ!!ምንም አቅም የሌላቸው እናት ደነገጡ! 3000,000(3ሚሊዮን ብር) ያስፈልጋል ሲባል ደግሞ ልጄ እያየኋት ልትሞትብኝ ነው ብለው
ተስፋ ቆረጡ

ባለፉት 3ወራት ጊዜ ውስጥ #ከ13ጊዜ በላይ ደም ያስፈለጋት ነቢ ግራገብቷት " #እባካችሁ_አድኑኝ
እያለች የሰቀቀን ቀኖቿን በለቅሶ እያሳለፈች ነው!!

እናንተ ደጋጎች ከተባበርን ከአምላክ ጋር እህታችንን እናድናታለን!ምንም ማድረግ ካልቻልን እየፀለይንላት በዱዓችን እያሰብናት #ሼር_SHARE በማድረግ ለብዙዎች እናድርስላት
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"
#አካውንት
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000441500665-ፋጡማ ሰኢድ(እህት)
ዘምዘም ባንክ
0002458120101-ፋጡማ ሰኢድ
#ስልክ
0934461899-ፋጡማ ሰኢድ
0901085189-ሩቅያ ሰኢድ
#ባይሽ_ኮልፌ_በጎ_አድራጎት