Get Mystery Box with random crypto!

ብዙነሽ ደመረው እባላለሁ፡፡ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ 2011 በውኃ ምህንድስና እና በሃይድሮሊክ | Lersha App

ብዙነሽ ደመረው እባላለሁ፡፡ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ 2011 በውኃ ምህንድስና እና በሃይድሮሊክ የትምህርት ዘርፍ በዲግሪ ተመርቂያለሁ፡፡ የመኖሪያ አድራሻዬ ሁሩታ ወረዳ ጎንዴ ቆርጫሳ ቀበሌ ሲሆን ከልጅነቴ ጀምሮ በቤተሰቦቼ የእርሻ ማሳ ላይ የተለያዩ የግብርና ተግባራትን በማከናወን ቤተሰቦቼን እረዳለሁ፡፡ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በውኃ ኢንጂነሪንግ የታወቀ ዩኒቨርስቲ ሲሆን እኔ በአካባቢያችን ጥቅም ላይ ያልዋለዉን የዉሃ ሃብት በዉጤታማነት ጥቅም ላይ ለማዋል ከነበረኝ ፍላጎት አንጻር በዚህ ዩንቨርሲቲ መማሬ ይህን ህልሜን ወደፊት እዉን ለማድረግ ታላቅ አጋጣሚ ሆኖልኛል፡፡ ከተመረኩኝ በኋላ በምኖርበት አካባቢ ሥራ የማግኘት እድል ባለማግኘቴ ሳስበዉና ስመኘዉ የነበረዉን የአካባቢያቸን አርሶ አደሮቸ መሰረታዊ የሆነ ችግር ለመቅረፍ የበኩሌን አስተዋጽኦ ማበርከት አልቻለኩም ነበር፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት ከለእርሻ ጋር መስራት በመቻሌ በለእርሻ በኩል የአርሶ አደሩን ማህበረሰብ ለማገልገል የነበረኝን ህልም እዉን በማድረግ በአርሶ አደራችን ላይ የተጫነዉን የረዥም ዘመን የግብርና ችግር ለማቃለል እችል ዘንድ ከለእርሻ ጋር ጠንክሬ እሰራለሁ፡፡

@LershaApp