Get Mystery Box with random crypto!

ስሜ ሸዋዬ ረጋሳ ይባላል፡፡ የምኖረው ጢዮ ወረዳ ላይ ሲሆን ከሜንሽን ፎር ሜንሽን አግሮ ቴክኒ | Lersha App

ስሜ ሸዋዬ ረጋሳ ይባላል፡፡ የምኖረው ጢዮ ወረዳ ላይ ሲሆን ከሜንሽን ፎር ሜንሽን አግሮ ቴክኒክ ኮሌጅ (ሀረር) በግብርናዉ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ተመርቂያልሁ፡፡ ከተመረቅሁ በኋላ ሥራ ለማግኘት እጅግ ተቸግሬ የነበረ ቢሆንም በንቃት በተመረቅኩበት ዘርፍ ስራ ስፈለግ ቆይቻለሁ፡፡ በአካባቢያችን የግብርናዉ መስክ ዝቅተኛ ደመወዝ የሚከፈልበት የሥራ ዘርፍ ተደርጎ ሲታሰብ ቢቆይም ለእርሻ በአካባቢያችን ስራ ሲጀምር ይህን ትርክት ታሪክ አድርጎታል፡፡ እኔም ለእርሻ ባወጣዉ የለእርሻ ወኪልነት የስራ ዘርፍ በጉጉት በመወዳደር ዕድሉን በማግኘቴ የፕላትፎርሙ ዋነኛ ተግባራት የሆኑትን የእርሻ ግብዓት ፣ የሜካናይዜሽን አገልግሎት እና የግብርና-የአየር ንብረት ምክሮችን በማቅረብ አርሶ አደሩን በማገልገልና የኔንም የፋይናንሽያል አቅም በማጎልበት ከእኔም አልፌ ወላጆቼንም መደገፍ ችያለሁ ፡፡ ለወደፊቱም ከለእርሻ ባገኘኋቸው ልምዶች በመጠቀም የራሴን የግብርና ግብዓት ማቅረቢያ ለመክፈት አቅጃለሁ ፡፡
@Lersha