Get Mystery Box with random crypto!

ማጣት - በማግኘት ህመም - በጤና ሀዘን    - በደስታ ውርደት -በዝና ክርምት እና በጋ ይፈራረ | MEGHFIRA👑

ማጣት - በማግኘት
ህመም - በጤና
ሀዘን    - በደስታ
ውርደት -በዝና

ክርምት እና በጋ ይፈራረቃሉ
ጨረቃ እና ፀሐይ ቦታ ይላቀቃሉ
ከቶ አይሻርም የአላህ ህግ ቃሉ
አልሃምዱሊላህ ሁሉም ያልፋል በሉ

በአንድ ሰሞን ኡዙር ወረርሽኝ ቢዛመት
የሰማይ ዳመና ቢሸሽ አንድ አንድ አመት
ሁሉም በየፈርጁ አደራጅ ቀማሪ
ያልፋል ከለመኑት አላህ ነው መሃሪ

ያልፋል ችግሩ ያልፋል
ያልፋል ጭንቀቱ ያልፋል
ያልፋል ከታገሰ ሆድ ካገር ይሰፋል
    
            ያልፋል - በመሀመድ አወል ሳላህ (አላህ ይዘንለት)
.
መልካም ቀን
.
@MEGHFIRA