Get Mystery Box with random crypto!

እንቅልፍ ማጣት (Insomnia) ምንድን ነው? ክፍል 1 **** ከረጅም አድካሚ ውሎ በኋላ ሰላም | 21St C. Soul

እንቅልፍ ማጣት (Insomnia) ምንድን ነው?
ክፍል 1
****
ከረጅም አድካሚ ውሎ በኋላ ሰላም ያለው እንቅልፍ እንደመትኛት አስደሳች ነገር አለ? ነገር ግን አብዛኞቻችን በእንቅልፍ እና እረፍት ማጣት እንሰቃያለን፡፡ እንቅልፍ ማጣት (Insomnia) በጣም የተለመደ የእንቅልፍ ችግር ነው:: ሙሉ ሌሊት ለመተኛት እድሉ ቢኖራችሁም እንቅልፍ ለመውሰድ ወይም ተኝቶ ለመቆየት ስንቸገር የሚከሰት ነው፡፡ የእንቅልፍ ማጣት መንስኤዎች፣ ምልክቶች እና ክብደት ከሰው ሰው ይለያያሉ። እንቅልፍ ማጣት የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል-
• እንቅልፍ የመተኛት ችግር
• ሌሊቱን ሙሉ ተኝቶ ለመቆየት መቸገር
• በጣም በማለዳ ከእንቅልፍ መነሳት
እንቅልፍ ማጣት(Insomnia) ሁለቱንም የእንቅልፍ መዛባት እና ቀን ቀን የሚታዩ ምልክቶችን ያጠቃልላል።እንቅልፍ ማጣት የሚያስከትላቸው ውጤቶች በሁሉም የሕይወትዎ ዘርፍ ማለት በሚያስችል ሁኔታ ሊጎዳ ይችላል።ጥናቶች እንደሚያሳዩት እንቅልፍ ማጣት በስራ አፈፃፀም ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር፣ የውሳኔ አሰጣጥን እንደሚያሳጣ እና ግንኙነቶችን ሊያበላሽ ይችላል።እንቅልፍ ማጣት ስሜትዎን ሊጎዳ እና ሌሎች የሕክምና ሁኔታዎችን ለመቆጣጠር የበለጠ ከባድ ሊያደርገው ይችላል።በአብዛኛዎቹ ሁኔታዎች የእንቅልፍ ማጣት ችግር ያለባቸው ሰዎች አጠቃላይ የህይወት ጥራታቸው የተዛባ እንደሆነ ያመለክታሉ።
ሁሉም ሰው አልፎ አልፎ ጥሩ እንቅልፍ ያጣል።ይህ ማለት እንቅልፍ ማጣት አለብዎት ማለት አይደለም።በአብዛኛዎቹ ሁኔታዎች በጣም ዘግይተህ ተኝተሃል፣ በጣም ቀደም ብለህ ተነስተህ ወይም በእኩለ ሌሊት ከእንቅልፍህ ነቅተህ ሊሆን ይችላል።ውጥረት/ጭንቀት የአንድ ምሽት ደካማ እንቅልፍ የተለመደ መንስኤ ነው፡፡
በቀጣይ ክፍል፡የእንቅልፍ ማጣት መንሳኤዎችና መፍትሄዎቻቸው፡፡
ኢምፓክት ኢትዮጵያ/ ነሐሴ 9/2014