Get Mystery Box with random crypto!

ዩኒቨርስቲዎችን መልሶ ለመክፈት የሚያስችል የዝግጅት ምዕራፍ ግምገማ በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች እየተካሄ | የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር

ዩኒቨርስቲዎችን መልሶ ለመክፈት የሚያስችል የዝግጅት ምዕራፍ ግምገማ በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች እየተካሄደ ነው፡፡

ዩኒቨርስቲዎችን መልሶ ለመክፈት ውሳኔ ላይ መደረሱን ተክትሎ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተቋቋመ ግብረኃይል ዩኒቨርስቲዎቹ ያሉበትን የዝግጅት ሁኔታ በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ እንዲቻል የመስክ ግምገማ እያካሄደ ይገኛል።

ግብረኃይሉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከጤና ሚኒስቴር ጋር ሆኖ ባዘጋጀው የዝግጅት ፕሮቶኮል መሰረት የዩኒቨርስቲዎቹን የዝግጁነት ሁኔታ ይገመግማል፡፡

ማንኛውም ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን መቀበል የሚያስችል ሁኔታ ላይ መሆን አለመሆኑ የሚታወቀው በመስክ ግምገማው በተጠናቀረው መረጃ መሰረት ሲሆን ውጤቱ ግምገማው ከተጠናቀቀ በኃላ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይገልጻል።

@MoSHEOfficial