Get Mystery Box with random crypto!

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እስከ ጥቅምት 11/2013 ዓ.ም ዝግጅት እንደ | የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እስከ ጥቅምት 11/2013 ዓ.ም ዝግጅት እንደሚያጠናቅቅ አስታወቀ

የ2013 የትምህርት ዘመን የመደበኛ ተማሪዎችን መልሶ መቀበል በሚቻልበት አግባብ ከካውንስል አባላት ጋር ምክክር ተካሄደ።

ለመማር ማስተማር ስራው ወሳኝ የሆነውን "ሰላምና ደህንነት" የማስጠበቁ ስራም ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚተገበር በውይይቱ ተጠቁሟል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎችን መልሶ ለመቀበል እንዲያስችል ዩኒቨርሲቲዎች ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ሀገራዊ አቅጣጫ ማስቀመጡ ይታወቃል።

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲም በቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ በተማሪዎች መልሶ ቅበላ እየተሰሩ ያሉ ተግባራትን በተመለከተና ትኩረት በሚሹ ጉዳዬች ዙሪያ በትላንትናው እለት ከዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት ጋር በተማሪዎች መመረቂያ አዳራሽ ውይይት አካሂደዋል።

በዩኒቨርሲቲያችን የተማሪዎች መልሶ ቅበላ ውጤታማ እንዲሆን ለማስቻል የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚደረገው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ በተቀናጀ እና በተደራጀ መልኩ እንዲተገበር የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በየተመደበበት የስራ ዘርፍ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚኖርበትም አቅጣጫ ተቀምጧል።

ኮሮና በሽታ በመማር ማስተማር ስራው ላይ አንዳች አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳይኖረው እና ተማሪዎችም ያለ ምንም ስጋት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ለማስቻል ተገቢውን የቅደመ ጥንቃቄ ስራ ለመስራት የሚያስችሉ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑም በውይይት መድረኩ ተገልጿል።

እስከ ጥቅምት 11/2013 ዓ.ም ድረስ በቅድመ ዝግጅት ምእራፍ ተግባራዊ መደረግ ያለባቸው ስራዎች በተገቢው እንዲጠናቀቁ በውይይቱ አቅጣጫ ተቀምጧል።

የኮሮና በሽታ በመከላከልና በመቆጣጠር ተማሪዎችን መልሶ ከመቀበል ባሻገር፤ ለመማር ማስተማር ስራው ወሳኝ የሆነውን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቁ ስራም ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚተገበርም በውይይቱ ተጠቁሟል።

እንደ ተቋም የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎችን መልሶ በመቀበል ረገድ ያስቀመጠውን አቅጣጫ በመከተል ለተማሪዎች ብቁ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ እንዲቻል በሁሉም መስክ ዝግጅቱ እስከ ጥቅምት 11/2013 ዓ.ም ድረስ እንዲጠናቀቅ በመድረኩ በምክክር መድረኩ አቅጣጫ ተቀምጧል።

በዩኒቨርሲቲው ሶስቱም ካምፓሶች ተማሪዎችን መልሶ ለመቀበል እንዲቻል የተለያዩ ኮሚቴዎች ተዋቅረው ወደ ስራ እንደተገባም በውይይቱ ተጠቅሷል።

@MoSHEOfficial