Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ቤቶችን የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም በማሳደግ የትምህርት ተደራሽነትና ጥራትን ለማስጠበቅ | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

ትምህርት ቤቶችን የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም በማሳደግ የትምህርት ተደራሽነትና ጥራትን ለማስጠበቅ እየተሰራ ነው
-----------------------------
ሚያዚያ 20,2015ዓ.ም ( የትምህርት ሚኒስቴር) የትምህርት ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን አስመልክቶ ከክልልና ከተማ መስተዳደር ለተውጣጡ የትምህርት ባለሙዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል።

የአቅም ግንባታ ስልጠናው ትምህርት ሚኒስቴር ከዩኔስኮ-ሁዋዊ (UNESCO - Huawei) ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ነው የተሰጠው።

በስልጠናው ላይ የተገኙት የዩኔስኮ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ዳይሬክተር ሪታ ቢሶናዝ (ዶ/ር) ስልጠናው ለትምህርት ባለሙያዎች በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ ያላቸውን ክፍተት ለመሙላት አጋዥ መሆኑን ገልፀዋል።

በትምህርት ቴክኖሎጂ በቂ እውቀት ያላቸውን የትምህርት ባለሙያዎችን በማፍራት እና ት/ቤቶችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በመገንባት የትምህርት ተደራሽነትና ጥራትን ለማስጠበቅ የሚደረገውን ርብርብ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ተወካይ አቶ ከድር ኡርጂ በበኩላቸው የትምህርት ስርአቱን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በተጠናከረ መልኩ ለመደገፍ የሚያስችሉ ስራዎችን በትኩረት እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር እያከናወናቸው ካሉ የለውጥ ስራዎች መካከል አንዱ ዲጂታላይዜሽን ሲሆን በዘርፉም በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot