Get Mystery Box with random crypto!

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በሀገር አቀፍ  የዩኒቨርሲቲዎች አምሳለ ችሎት ውድድር አሸነፈ በደብረ ማርቆስ | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በሀገር አቀፍ  የዩኒቨርሲቲዎች አምሳለ ችሎት ውድድር አሸነፈ

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ  እና በፌደራል ፍትህ እና ህግ ኢንስቲትዩት ትብብር ሲካሄድ የቆየው 7ኛው አገር አቀፍ የኢትዮጵያ የህግ ትምህርት ቤቶች  የምስለ-ችሎት  ውድድር በጎንደር ዩኒቨርስቲ አሸናፊነት ተጠናቋል።

በፍጻሜ ውድድሩ አዘጋጁ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲ 2ኛ እንዲሁም ድሬደዳዋ ዩኒቨርሲቲ የ3ኛ ደረጃን ይዘው በማጠናቀቅ የዋንጫና የሜዳልያ ተሸላሚ ሆነዋል።

ጎንደር ዩኒቨርስቲን ወክለው የተወዳደሩት የ5ኛ አመት የህግ ተማሪ የሆኑት ሰላማዊት አሰፋ፣  ኢያሱ ጨቅሉ እና  መክሊት ጌጡ ሲሆኑ አሰልጣኛቸው ደግሞ የህግ መምህር የሆነው አቶ ሃይለማርያም በላይ ናቸው።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot