🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የግል ትምህርት ቤቶች የክፍያ ጭማሪ እያማረራቸው መሆኑን ወላጆች ተናገሩ ለኢቲቪ አስተያየታቸውን | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

የግል ትምህርት ቤቶች የክፍያ ጭማሪ እያማረራቸው መሆኑን ወላጆች ተናገሩ

ለኢቲቪ አስተያየታቸውን የሰጡት ወላጆች፣ ገቢያችን ሳይጨምር በየዓመቱ የሚደረገው የትምህርት ቤቶቹ ጭማሪ ከአቅም በላይ ሆብናል፤ እዚህ ላይ ቁጥጥር መደረግ አለበት ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ የግል ትምርት ቤቶች አሠሪዎች ማኅበር በበኩሉ፣ ትምህርት ቤቶቹ በኮቪድ በደረሰባቸው ከፍተኛ ኪሳራ እና በ2015 ዓ.ም ጭማሪ እንዳያደርጉ መከልከላቸው ገበያው ላይ ለመቆየት የግድ ጭማሪ ለማድረግ እንሚያስገድዳቸው ገልጿል።

ትምህርት ቤቶች ዝግ በሚሆኑበት ሐምሌ እና ነሐሴ ለመምህራን የሚከፈለው ክፍያም ግንዛቤ ውስጥ መግባት አለበት ያለው ማህበሩ ግብአቶችን ለማቅረብ አሁን ያለው የገበያ ዋጋ ትልቅ ተግዳሮት መሆኑንም ገልጿል።

በዚህም የተሻለ የትምህርት አካባቢን ለመፍጠር እና የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እንዲሁም የሚፈልገውን ትርፍ አግኝተው በገበያው ውስጥ ለመቆየት የክፍያ ማስተካከያ ግዴታ ነው ብሏል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot