🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከተለያዩ አገራት የትምህርት ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ ረቡዕ ግንቦት 2 ቀን | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከተለያዩ አገራት የትምህርት ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ

ረቡዕ ግንቦት 2 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከአለም አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ጎን ለጎን ከተለያዩ አገራት የትምህርት ሚኒስትሮች ጋር የፓናል ውይይት አካሂደዋል።

በውይይታቸውም ኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፉ ላይ እያደረገችው ያለውን ለውጥ እና ሥራ ያብራሩ ሲሆን፤ በአጠቃላይ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝም አንስተዋል።

የዘንድሮው አለም አቀፍ የትምህርት ጉባኤ <<አዲስ ጅማሮ፡ የመማር ባህልን ማሳደግ፣ የመቋቋም አቅምን መገንባት፣ ዘላቂነትን ማሳደግ። በንድፍ ሃሳብ የተደገፈ ጠንካራና የተሻለ ትምህርት>> በሚል መሪ ቃል በብሪታኒያ እየተካሄደ ይገኛል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ፤ በትናንትናው ዕለት ከብሪታኒያ የልማትና የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አንድሪው ሚቼል እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የልጃገረዶች ትምህርት ልዩ መልዕክተኛ ከሆኑት ሄለን ግራንት ጋር በትምህርት ዘርፍ ያለውን ትብብር የበለጠ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውም ተገልጿል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot