🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የማላዊ ፍርድ ቤት ተማሪዎች ጸጉራቸዉን ድሬድ ማድረግ እንዲችሉ ፈቀደ በማላዊ የሚገኘው ከፍተኛ ፍ | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

የማላዊ ፍርድ ቤት ተማሪዎች ጸጉራቸዉን ድሬድ ማድረግ እንዲችሉ ፈቀደ

በማላዊ የሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤት የትምህርት ባለስልጣናት በሀገሪቱ ውስጥ ባሉ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ጸጉራቸዉን ድሬድ ያደረጉ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ እንዲገቡ ፍቃድ ሰጥቷል፡፡ፍርድ ቤቱ በ2016 እና 2010 ዓመት ወደ ህዝብ ትምህርት ቤት ለመግባት የተከለከሉ ሁለት የራስተፈሪያን ልጆች ባቀረቡት አቤቱታ ላይ በዞምባ ከተማ ባስቻለዉ ችሎት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

የሁለቱ ተማሪዎች ጉዳይ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ካገኙ በኋላ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል።በማላዊ የሚገኘው የራስተፈሪያን ማህበረሰብ እና የሀገሪቱ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጉዳዩን ለመፍታት የተካሄደው ውይይት ባለመሳካቱ የተራዘመ የህግ ክስ ቀርቦ ውሳኔው ሰኞ እለት ተላልፏል።

ዳኛ ንታባ ድሬድ ያደረጉ ህጻናት ትምህርት ቤት እንዳይማሩ መከልከል የመማር መብታቸውን መጣስ ነው ሲሉ ውሳኔ አስተላልፈዋል።"የትምህርት ሚኒስቴር ሁሉም የራስተፋሪያን ማህበረሰብ ልጆች ድሬድ አድርገዉ በክፍል ውስጥ እንዲገቡ ለመፍቀድ መግለጫ ማውጣት አለበት ይህንኑ የሚገልጽ መመሪያ እስከ ሰኔ 30 ድረስ ማሳወቅ እንደሚኖርበት" ዳኛ ንታባ አዘዋል፡፡

ይህዉ ጉዳይ በሀገሪቱ ውስጥ በሚገኙ የራስተፈሪያን ማህበረሰብ ስም በሶስት የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች አማካይነት ወደ ፍርድ ቤት ሊቀርብ ችሏል፡፡

Via ዳጉ ጆርናል

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot