Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ በርካታ ትምህርት ቤቶች ከ20 እስከ 100 ፐርሰንት የሚደርስ የትምህርት ክፍያ ጭማሪ | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

በአዲስ አበባ በርካታ ትምህርት ቤቶች ከ20 እስከ 100 ፐርሰንት የሚደርስ የትምህርት ክፍያ ጭማሪ ለማድረግ የውሳኔ ሃሳብ ማቅረባቸውን "ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ዘግቧል። የከተማዋ የትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን ግን፣ የትኛውም ትምህርት ቤት ከተማሪ ወላጆች ጋር ስምምነት ላይ ሳይደርስ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ እንደማይችል ማስጠንቀቁን ዘገባው ጠቅሷል። በከተማዋ ከሚገኙት 1 ሺህ 558 ትምህርት ቤቶች መካከል፣ በቀጣዩ ዓመት የትምህርት ክፍያ ጭማሪ ለማድረግ መወሰናቸውን ለባለሥልጣኑ ያሳወቁት፣ 1 ሺህ 257 ትምህርት ቤቶች እንደኾኑ ባለሥልጣኑ መናገሩን ዜና ምንጩ አመልክቷል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot