Get Mystery Box with random crypto!

በተጋነነ የክፍያ ጭማሪ ምክንያት ትምህርትቤቶችና ወላጆች ለሁለት ተከፈሉ! የግል ትምህርት ቤቶች | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

በተጋነነ የክፍያ ጭማሪ ምክንያት ትምህርትቤቶችና ወላጆች ለሁለት ተከፈሉ!

የግል ትምህርት ቤቶች ለ2016 ዓም የትምህርት ዘመን የጠየቁት ከፍተኛ የክፍያ ጭማሪ ወላጆችና ትምህርት ቤቶች ለሁለት ተከፍለዋል።

በአዲስ አበባ ካሉ 1558 የግል ትምህርት ቤቶች፣ ጭማሪውን ለማድረግ ፍላጎት ያሳዩት  1253 ትምህርት ቤቶች ቢሆኑም፣  1031 ትምህርት ቤቶች ብቻ ከወላጆች ጋር ስምምነት ላይ  ቢደርሱም 226ቱ መስማማት እንዳልቻሉ፣  የትምህርት ስልጠናና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።ባለስልጣኑ ይህንን ያስታወቀው ዛሬ ሐሙስ ግንቦት 3 ቀን 2015 ዓም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ እንደገለፁት፣ በአዲስ አበባ ከሚገኙት 1558 የግል ትምህርት ቤቶች 1253 የክፍያ ጭማሪ ለማድረግ ፍላጎት አሳይተዋል።226 ትምህርት ቤቶች ጋር  መግባባት ላይ መድረስ ያልተቻለ ቢሆንም፣  በቀጣይ መግባባት እንዲፈጠር ባለስልጣኑ ውይይት የሚያደርግ መሆኑን አስረድተዋል።

በሌላ በኩል ከ2016 ዓም የትምህርት ዘመን ጀምሮ ማንኛውም የግል ትምህርት ቤቶች ከወርሃዊ ክፍያ ውጭ በአይነትም ሆነ በገንዘብ ጭማሪ ማድረግ እንደማይችሉ አክለው ገልፀዋል።በአሁኑ ወቅት ጭማሪ ለማድረግ መግባባት ላይ የደረሱት ትምህርት ቤቶች፣ ከ20 በመቶ ጀምሮ ጭማሪ ለማድረግ መወሰናቸውን አቶ ዳኘው ተናግረዋል።

Vi Reporter


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT