Get Mystery Box with random crypto!

#Update መላው የመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ትላንት በደረሰው አሰቃቂ የመኪና አደጋ ከባድ | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

#Update

መላው የመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ትላንት በደረሰው አሰቃቂ የመኪና አደጋ ከባድ ሀዘን ውስጥ እንደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት ዶ/ር ኢብራሂም ከሊል ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

አደጋው ትላንት 1 ሰዓት ከ20 ላይ በዶዶላ ማዕከል ለማስተማር መምህራንን ይዞ ሲጓዝ የነበረ አውቶብስ " ሰብስቤ ዋሻ " የሚባል አካባቢ ገደል ውስጥ ገብቶ መድረሱን ያብራራቱ ፕሬዜዳንቱ " አደጋው እጅግ በጣም አሰቃቂ ነበር " ብለዋል።

አደጋው እንዴት ሊደርስ ቻለ በሚለው ጉዳይ ላይ ከቴሌቪዥን ጣቢያው የተጠየቁት ዶ/ር ኢብራሂም " መኪናው ገደል ውስጥ የገባበት ቦታ በተደጋጋሚ መሰል አደጋዎች የሚደርሱበት ቦታ ነው ፤ አሁን ባለው ሁኔታ ከአደጋው የተረፉና ህክምና ላይ ያሉ መምህራኖቻችን ናቸው እንዴት የተፈጠረ የሚለውን መረጃውን መስጠት የሚችሉት " ብለዋል።

" በአካባቢው ላይ የነበሩ ሰዎች ግን መኪናው አደገኛ ኩርባ አለች እሱን ጨርሶ እንደወረደ ቀጥታ እንደገባ ነው የነገሩን " ሲሉ አክለዋል።

በአደጋው እስካሁን የ20 መምህራን ህይወት ማለፉን የገለፁት ዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት በአስጊ ሁኔታ ላይ ያሉ መኖራቸውን ተናግረዋል።

ከጉዳት የተረፉ በዶዶላ፣ ሻሸመኔ፣ ሀዋሳ ሆስፒታሎች ህክምና ላይ የሚገኙ መሆናቸውን አመልክተዋል። በህክምና ላይ ካሉት ቀላል ጉዳት እንዲሁም ከባድ ጉዳት የደረደባቸው ያሉ ሲሆን ተቋሙ እነሱን እየተከታተለ ይገኛል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት ህይወታቸው ያለፈውን ወደ ጎባ ሆስፒታል የመመለስ ስራ መሰራቱን ጠቁመው " በብዛት የባሌ አካባቢ ተወላጆች ስለሆኑ መሟላት ያለባቸው ሁኔታዎች ተሟልተው ቤተሰቦቻቸው ወስደወል፤ ራቅ ራው ካሉ አካባቢዎች የመጡ መምህራኖቻችንን ዩኒቨርሲቲ ደረጃ ሽኝት እንዳረጋለን " ሲሉ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ተቋሙ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባሰራጨው የሀዘን መግለጫ ለማስተማር ወደ ዶዶላ ከተማ በመጓዝ ላይ እያሉ ተሸከርካሪው መንገድ በመሳት በተፈጠረው አደጋ የዩኒቨርስቲው #መምህራን፣ #ሠራተኞች እና #ተማሪዎች ህይወታቸው ማለፉን ገልጿል።

28 የሚሆኑ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው በተለያዩ ሆስፒታሎች በህክምና ላይ ይገኛሉ ብሏል።

ዩኒቨርሲቲው አደጋው ከደረሰበት ሰዓት ጀምሮ አብረውት ለነበሩት የምዕራብ አርሲና የባሌ ዞኖች፣ የሻሸመኔ፣ አዳባ፣ ዶዶላና ሮቤ ከተሞች ነዋሪዎችና አመራሮች ዩኒቨርስቲው አመራርና ሠራተኞች በተለይ አደጋው የተፈጠረበት አከባቢ ነዋሪዎች ምስጋና አቅርቧል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot