Get Mystery Box with random crypto!

አዲሱን ስርዓተ ትምህርት መሰረት አድርጎ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጠው የ2015 ዓ.ም የ6ኛ ክ | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

አዲሱን ስርዓተ ትምህርት መሰረት አድርጎ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጠው የ2015 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በዛሬው እለት በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 182 የመፈተ ኛ ጣቢያዎች መሰጠት ጀመረ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከምክትል ቢሮ ኃላፊው ከአቶ አሊ ከማል እና ከየካ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ከአቶ ፈይሳ ወዳጆ ጋር በመሆን በክፍለከተማው በሚገኙ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተዘዋውረው የፈተናውን አጀማመር ተመልክተዋል።

የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዘንድሮ እንደመጀመሩና ፈተናውን የሚወስዱ ተማሪዎች በእድሜ አነስተኛ እንደመሆናቸው ቢሮው ፈተናው ያለምንም ችግር እንዲጠናቀቅ የጸጥታ አካላትን ጨምሮ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ሲሰራ መቆየቱን የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ገልጸው በከተማ አስተዳደሩ ላለፉት ሁለት ቀናት የተካሄደው የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ያለምንም እንከን መጠናቀቁን በመጥቀስ የ6ኛ ክፍል ፈተናም በተመሳሳይ ሁኔታ ያልምንም ችግር እንዲጠናቀቅ ሁሉም የፈተና አስፈጻሚ ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ዘንድሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ182 የፈተና ጣቢያዎች 75,090 ተማሪዎች የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ መመዝገባቸው ቀደም ብሎ መገለጹ ይታወቃል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot