🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ሁለት የአስራ አንደኛ ክፍል ተማሪዎች ለስምንተኛ ክፍል ሚኒስትሪ ተፈታኞች ለመፈተን ሲሞክሩ በቁጥጥ | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

ሁለት የአስራ አንደኛ ክፍል ተማሪዎች ለስምንተኛ ክፍል ሚኒስትሪ ተፈታኞች ለመፈተን ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ

በደቡብ ብሔር ብሔረሶባችና ህዝቦች ክልል ፈተና በተሰጠባቸዉ በሁሉም ማዕከላት ፈተናዉ ያለምንም የፀጥታ ችግር የተጠናቀቀ ሲሆን በደቡብ ኦሞ ዞን ሁለት የአስራ አንደኛ ክፍል ተማሪዎች ለሌላ ሰዉ ለመፈተን በመሞከራቸዉ ፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው አስታውቋል ።

ተፈታኝ ሆነው ነገር ግን ሌላ ሰው እንዲፈተንላቸው አይዲ ቁጥራቸዉ ሰጥተዉ የላኩ ሁለት ተማሪዎችን ጨምሮ አራት ሰዎች በቁጥጥር ስር ዉለዉ ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ኃላፊ የሆኑት ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል ።

ፖሊስ ኮሚሽኑ ተፈታኞችን የሚረብሽና ፈተናዉ እንዳይስተጓጎል በማድረግ የፀጥታ ችግር እንዳያጋጥም እና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ለተባበሩ ሁሉ  ምስጋናውን አቅርቧል ። ክልል አቀፍ የስምንተኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና በሁሉም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች ከሰኔ 26 እስከ ሰኔ 27 ቀን 2015 ዓ.ም ተሰጥቶ መጠናቀቁ ይታወሳል ።


ዳጉ ጆርናል


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT