Get Mystery Box with random crypto!

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ዙር የ12ተኛ ክፍል የ2015 ዓ.ም ተፈታኝ ተማሪዎችን እየተቀበለ | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ዙር የ12ተኛ ክፍል የ2015 ዓ.ም ተፈታኝ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው።

መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና ከስርቆት ነጻ የሆነ ፈተና ለመስጠት የ12 ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ከየሚማሩበት ትምህርት ቤት ወጣ ብሎ በመንግስት የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ መሰጠት ከጀመረ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡለትን የመጀመሪያው ዙር የ12ተኛ ክፍል የሶሻል ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ይገኛል።

የቅበላ ሂደቱም ከዛሬ የሚጠናቀቅ ይሆናል።

ሐምሌ18/2015 ዓ.ም አጠቃላይ ስለፈተናው ሁኔታ ለተማሪዎች ኦሬንቴሽን ተሰጥቶ ከሐምሌ 19 እስከ 21/2015 ዓ.ም የመጀመሪያው ዙር የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ይጠበቃል።

ዉድ ተማሪዎቻችን እንኳን ወደ ውቢቷ ወልድያ ከተማና ዩኒቨርሲቲ በሰላም መጣችሁ በማለት ዩኒቨርሲቲው መልካም ዕድል ተመኝቷል።

#አሚኮ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT