Get Mystery Box with random crypto!

ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የ2015 ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ ሥነ ስርዓት ተሰርዘ በክልሉ ባለ የፀጥታ ች | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የ2015 ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ ሥነ ስርዓት ተሰርዘ

በክልሉ ባለ የፀጥታ ችግር ምክንያት የ2015 ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ በዓል መሰረዙን የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል።

የምረቃ በዓሉን ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም ለማድረግ ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ቢሆንም በክልሉ በተከሰተው የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት የምረቃ ፕሮግራሙ መሰረዙን የተቋሙ የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት ከተማ ጥላሁን (ዶ/ር) ገልፀዋል።

"ተማሪዎቻችንን ለማስመረቅ ተዘጋጅተን ነበር፤ ይሁን እንጂ ሰው እየሞተ የምረቃ በዓል ማድረግ ትርጉም አይኖረውም" ብለዋል ምክትል ፕሬዝዳንቱ።

የተቋሙ አንድ ተማሪ እና አንድ መምህር ህይወታቸው ማለፉን የገለጹት ዶ/ር ከተማ፤ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የምረቃ በዓሉን ማከናወን እንዳልተቻለ ጠቁመዋል።

659 የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች እና ሁለት የሁለተኛ ዲግሪ ተመራቂዎች ትምህርታቸውን ማጠናቀቃቸው ተገልጿል።

ተመራቂዎቹ አሁን ላይ ጊዚያዊ ዲግሪ (Temporary) እየተሰጣቸው መሆኑን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ዩኒቨርሲቲው የተመደቡለትን ከ6 ሺህ በላይ የማህበራዊ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞችን ከትላንት ጀምሮ እየተቀበለ ይገኛል።

ትምህርታችሁን ላጠናቀቃችሁ የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT