🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2015 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ያሉበትን | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2015 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ያሉበትን ሁኔታ ተመለከቱ ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋና ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢና በ4 ኪሎ ሳይንስ ፋካሊቲ ተገኝተው የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና  ተፈታኝ ተማሪዎችን አበረታተዋል።

በዩኒቨርሲቲዎቹ ያለውን የተማሪ አቀባበል፣የመኝታና የመመገቢያ ቦታዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በምልከታቸውም ተፈታኝ ተማሪዎች ተረጋግተው ፈተናቸውን እንዲሰሩ ሚኒስትሩ አበረታተዋል ።

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሀምሌ 19 /2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ይታወቃል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT