Get Mystery Box with random crypto!

በአማራ ክልል በጸጥታ ችግር ምክንያት የባከነውን የትምህርት ጊዜ ለማካካስ የዓመቱን የመማር ማስተማ | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

በአማራ ክልል በጸጥታ ችግር ምክንያት የባከነውን የትምህርት ጊዜ ለማካካስ የዓመቱን የመማር ማስተማር ሒደት ለማሻሻል ጥናት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በክልሉ ምስራቅ፣ ምዕራብ እና ሰሜን ጎጃም ዞኖች እስካሁን ትምህርት አለመጀመሩን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) ለአሚኮ ተናግረዋል። 

በጸጥታ ሥጋት ምክንያት ከተገለፁት ዞኖች ውጭ በሚገኙ የክልሉ አካባቢዎች 60 በመቶ የአንደኛ ደረጃ እና 55 በመቶ የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች ብቻ በመማር ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

በክልሉ በየጊዜው ሰላም በሚኾንባቸው አካባቢዎች ከጸጥታ መዋቅሩ እና ከማኅበረሰቡ ጋር በመቀናጀት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ እንዲመለሱ እየተሠራ ነው ብለዋል።

የባከነውን የትምህርት ጊዜ ለማካካስ ቢሮው የዓመቱን የትምህርት ሥርዓት እንደገና ለማሻሻል ጥናት እያደረገ  እንደሚገኝም ኃላፊዋ ጠቁመዋል።

በተለይ በዚህ ዓመት የክልል እና ሀገር አቀፍ ፈተና ለሚወስዱ የ6ኛ፣ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የባከኑ ጊዜያትን በልዩ ሁኔታ ለመሸፈን ከመምህራን እና ርዕሰ መምህራን ጋር ውይይት እየተደረገ መኾኑን ገልጸዋል፡፡

አሚኮ

⊰  ㅤ    ⫹⫺ㅤ     ⎙ㅤ     ⌲ ⊱
࿙ ᴸⁱᵏᵉ    ˢᵘᵖᵖᵒʳᵗ    ˢᵃᵛᵉ     ˢʰᵃʳᵉ ࿚

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT