🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተመራቂ ተማሪዎች በጠዋቱ ደምቋል። ባሕር ዳር፡ ጥር 22/2013 ዓ.ም ( | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተመራቂ ተማሪዎች በጠዋቱ ደምቋል።
ባሕር ዳር፡ ጥር 22/2013 ዓ.ም (አብመድ) የደብረ ታቦር ዩንቨርሲቲ በ39 ትምህርት ክፍሎች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 518 ተማሪዎችን ለ7ኛ ጊዜ ዛሬ ያስመርቃል፡፡ ከተመራቂዎች ውስጥም 40 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው፡፡
የ7ኛ ዙር ተመራቂዎችም በመጀመሪያ ዲግሪ 2 ሺህ 486 (በመደበኛውና በኤክስቴንሽን መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ)፤ በሁለተኛ ዲግሪ 32 ተማሪዎች እንደሆኑ ከዩኒቨርሲቲው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ አመላክቷል።
የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ አቶ ዳዊት ብርሃኑ በተለይ ለአብመድ እንደገለጹት የዛሬ ተመራቂ ተማሪዎች በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የምረቃ ጊዜያቸው የተራዘመባቸው ናቸው።
እንደ አቶ ዳዊት ማብራሪያ ዩኒቨርሲቲው በ2012 ዓ.ም በሁለተኛው ግማሽ ዓመት በመደበኛና በተከታታይ የትምህርት መርሃ ግብሮች የሚማሩ 12 ሺህ 874 ተማሪዎች ነበሩት፡፡ ከነዚህ ውስጥም 4 ሺህ 690 ሴቶች ናቸው፡፡
ዩኒቨርሲቲው ዛሬ በሚያከናውነው የምረቃ መርሃ ግብርም በመደበኛው 1 ሺህ 905 (ወንድ- 1 ሺህ 207 ሴት-698) እንዲሁም በተከታታይ ትምህርት 581 (ወንድ-274 ሴት-305) ተማሪዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ይመረቃሉ፡፡
በኀይድሮሊክስ፣ በደቨሎፕመንታል ኢኮኖሚክስ፣ በአካውንቲንግ፣ በጆግራፊና ቴፍል ቀደም ሲል ሳይመረቁ የቀሩ 32 የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎችም በዚህ የምረቃ መርሃ ግብር ተካተዋል፡፡
ዩኒቨርስቲው 47 ትምህርት ክፍሎች አሉት፡፡ ለዛሬ ምረቃ ያበቃቸው ተማሪዎችም በ39 ትምህርት ክፍሎች ያሰለጠናቸውን ነው፡፡
ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በማህበራዊ ሳይንስና ሰብአዊ ፣ በተፈጥሮ ቀመርና ሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ በግብርና እና አካባቢ ሳይንስ ፋኩሊቲዎች፤ በጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና በሜዲስን ትምህርት ቤት የተዋቀረ የሶስተኛው ትውልድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ነው፡፡
የደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ በ2022 ዓ.ም በምርምር ሥራዎች፣ በአረንጓዴ ልማት፣ በማሕበረሰብ አገልግሎቶችና በሌሎችም ተግባራት ከኢትዮጵያ ምርጥ 10 ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ለመሆን እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝም የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ አቶ ዳዊት ተናግረዋል፡፡

Via AMMA

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT