Get Mystery Box with random crypto!

መቀሌ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ትምህርት ለማስጀመር መዘጋጀቱን አስታወቀ -------------------- | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

መቀሌ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ትምህርት ለማስጀመር መዘጋጀቱን አስታወቀ
-----------------------------------------
መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ተቀብሎ መደበኛ የመማር ማስተማሩን ሥራ ለማስጀመር ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ።

ዩኒቨርሲቲው የሚቀበላቸው ተማሪዎች ከ1ኛ እስከ 6ኛ ዓመት ድረስ የሚማሩ እንደሆነ ተመልክቷል።

የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር ዶክተር ከሰተ ለገሰ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው 13 ሺህ ተማሪዎችን ይቀበላል።

ተማሪዎችን ከአውቶቡስ መነኸሪያ እና መቀሌ ከተማ ተቀብለው ወደ ዩኒቨርሲቲ ለማስገባት የተማሪዎች ህብረት አመራሮች ተሽከርካሪዎች መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲው የሚቀበላቸው ተማሪዎች ያለምንም ችግር ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የምግብ ፣ መኝታ ፣ መማሪያ ክፍሎች የኤሌክትሪክ መብራት እና የንፁህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት መሰናዳታቸውን ዶክተር ከሰተ አስታውቀዋል።

የጊቢው የማፅዳት ስራ መጠናቀቁን አመልክተው የመማር ማስተማር ስራው የሚካሄደው የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል በሚያስችል መንገድ እንደሆነ አስረድተዋል።

ከሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች ለሚመጡ ተማሪዎች ከጥር 28 እስከ 30፣ 2013 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ የእንኳን ደህና መጣችሀ አቀባበል ይደረጋል ብለዋል።

ከአቀባበሉ በኋላ የመማር ማስተማሩ ሥራ እንደሚቀጥል አመልክተዋል።

ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ገብተው የመማሪ ማስተማር ስራ ሲጀመር በመልካም ሥነ-ምግባር ትምህርታቸውን መከታተል እንደሚጠበቅባቸውም አስታውቀዋል።
(ምንጭ፦ኢዜአ)

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT