Get Mystery Box with random crypto!

ለአምቦ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ አመት መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ የአምቦ ዩኒቨርሲቲ የአንደኛ አመት መ | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

ለአምቦ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ አመት መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

የአምቦ ዩኒቨርሲቲ የአንደኛ አመት መደበኛ ተማሪዎች ጥር 28 እና 29 ቀን 2013 አ/ም በግቢው በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ የወጣው ማስታወቂያ ያመለክታል።

ተማሪዎች በፊት በነበራችሁበት ካምፖስ በተጠቀሰው ቀን በአካል በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ እና የዲፓርትመንት ምደባችሁን ደግሞ ከጥር 26 ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው የኦንላይን አድራሻ estudent.ambou.edu.et ማየት ምትችሉ መሆኑን ይገልፃል።

ይህንንም ተከትሎ ከተቀመጠው ቀን ዘግይቶም ይሁን ቀድሞ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርቲው እንደማይቀበል ያሳስባል።

ተማሪዎች በኮሮና ወረርሺኝ ሳቢያ ለረጅም ጊዜ ከትምህርት ገበታቸው ርቀው ዳግም መንግስት ባስቀመጠው የመከላከል መርህ ተማሪዎች በጥንቃቄ የመከላከል መርሆችን እየተከተሉ ትምህርታቸውን መቀጠል እንደሚችሉ መወሰኑን ተከትሎ የአምቦ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ተመራቂ ተማሪዎችን ቀጥሎም ተመራቂ ያልሆኑ ተማሪዎችን ጥሪ በማድረግ የመማር ማስተማር ሂደቱን እያስቀጠለ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎችን ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መስፈርት ጥር 22 ቀን 2013 አ/ም ለማስመረቅ ዝግጅቱን አጠናቋል፤ይህንንም በማስመልከት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ከመቀነስ አንፃር ዩኒቨርሲቲው ባስቀመጠው የመከላከል መርህ ተመራቂ ተማሪዎች ግቢውን ከለቀቁ በኃላ የመጀመሪያ አመት ተማሪዎችን በመቀበል ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ በመወሰኑ የመጀመሪያ አመት ተማሪዎች ከላይ በተቀመጠላችሁ ጊዜ መሰረት በግቢው በመገኘት ትምህርታችሁን እንድትጀምሩ ዩኒቨርሲቲው ያሳስባል።

Via AUSUE

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ ተማሪ ነክ መረጃዎች ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT