Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚኒስቴር አሁንም ዝግጁ ነኝ እያለ ነው ሚኒስቴሩ በትግራይ ክልል ትምህርት ለማስጀምር | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

ትምህርት ሚኒስቴር አሁንም ዝግጁ ነኝ እያለ ነው

ሚኒስቴሩ በትግራይ ክልል ትምህርት ለማስጀምር ቅድመ ዝግጅቶች እያደረገ መሆኑን ገለጸ
----------
የትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል ትምህርት ለማስጀምር የሚያስፈልጉ ቅድመ ዝግጅቶች እያደረገ መሆኑን ገለጸ፡፡

በትግራይ ክልል በነበረው ህግ የማስከበር ተግባር በጸረ-ሰላም ሃይሎች የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ የመገንባት ስራ እየተሰራ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

በሚኒስቴሩ የትምህርት መሻሻል ዳይሬክተር ጀነራል ዮሐንስ ወጋሶ በተለይ ለዋልታ እንደገለጹት፣ የትመህርት ሚኒስቴር ትምህርት ለማስጀመር የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

ከክልሉ አስተዳደር ጋር በመሆን በተሰራው ውጤታማ ስራ በቅርቡ ትምህርት የሚጀመርባቸው አካባቢዎች እንደሚኖሩም አቶ ዮሐንስ ጠቁመዋል፡፡

በትግራይ ክልል የሚገኙ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችንም ለመፈተን የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራም እየተሰራ ስለመሆኑን ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይም በቤኒሻንጉል ክልል በመተከል ዞን በተከሰተው አለመረጋጋት ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው የተነሱ ተማሪዎች መኖራቸውን ያስታወሱት አቶ ዮሐንስ፣ ከጸጥታ አካላት ጋር ትምህርት ማስጀመር የሚያስችሉ ስራዎች በመሰራት ላይ ናቸው ብለዋል፡፡

የተለያዩ አጋር አካላትን ጭምር በማስተባበር የዝግጅት ምዕራፉ በፍጥነት ተጠናቆ በአካባቢው የመማር ማስተማር ሂደቱ በሚፈለገው ፍጥነት እንዲጀመር ይደረጋልም ነው ያሉት፡፡
(በሜሮን መስፍን)

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ ተማሪ ነክ መረጃዎች ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT