Get Mystery Box with random crypto!

#UPDATE የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በወረቀት እንደሚሰጥ ተገለፀ። ትምህርት ሚኒስቴር | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

#UPDATE
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በወረቀት እንደሚሰጥ ተገለፀ።

ትምህርት ሚኒስቴር በኦን ላይን ሊሰጥ የነበረውን የ2012ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በወረቀት እንደሚሰጥ አስታውቋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ) በኦንላይን ለመስጠት የታሰበው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በኮሮና ምክኒያት መፈተኛ ታብሌቶች በግዜ ወደ ሀገር ውስጥ መግባት ባለመቻላቸው ፈተናውን በወረቀት ለመስጠት መወሰኑን ገልፀዋል።

በዚህም መሰረት የ2012ዓ.ምሀገር አቀፍ ፈተና የካቲት 29, 2012ዓ.ም እንደሚሰጥ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

ከየካቲት 21-27,2013ዓ.ም ፈተናው እና የመልስ መስጫ ወረቀቶች ወደ ዞኖች እንደሚደርሱም በመግለጫው ላይ ተገልጿል።

የ2012ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በኦንላይን ለመስጠት ትምህርት ሚኒስቴር ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱ የሚታወስ ነው።

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT