🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለሚቀጥሉት ሦስት ሳምንታት በክልሉ ውስጥ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲ | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

የትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለሚቀጥሉት ሦስት ሳምንታት በክልሉ ውስጥ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ይቆያሉ
*********
(ኢ.ፕ.ድ)

የትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የ2012 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ለመውሰድ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ በየትምህርት ቤቶቻቸው ተገኝተው በጊዜያዊ አስተዳደሩ በኩል የሚሰጠውን መረጃ ይከታተላሉ ተባለ፡፡

ተማሪዎች በትግራይ ክልል ውስጥ ወዳሉት አራት ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚወሰዱናየስነ ልቦና እና የአካዳሚክ ማጠናከሪያ እንደሚሰጣቸው ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ለተማሪዎቹ የዲጂታል ምዝገባን ጨምሮ ለፈተና የሚያስፈልጉ ዝግጅቶች ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ከገቡ በኋላ ይከናወናል፤ ፈተናውንም የሚወስዱት በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ መሆኑ ተገልጿል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ እንደገለጹት፤ ፈተናው ከተጠናቀቀ በኋላ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ተማሪዎቹን በየትምህርት ቤቶቻቸው አካባቢ ያጓጉዛል፡፡

እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ፤ በክልሉ ያለውን የትምህርት ቤት መሰረተ ልማት ዳግም ለማደስና ወደ ትምህርት መስመር ለመመለስ ትምህርት ሚኒስቴር 236 ሚሊዮን ብር አስተላልፏል፡፡

በትግራይ ክልል 12 ሺህ ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሏል።

በዋለልኝ አየለ

Via EPA

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT