🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ትምህርት ሚኒስቴር በክልሎች ያለውን የፈተና አሰጣጥ ትኩረት ይስጠው Admin 4: ' ትናን | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

ትምህርት ሚኒስቴር በክልሎች ያለውን የፈተና አሰጣጥ ትኩረት ይስጠው


Admin 4:
" ትናንትና የ12ኛ ክፍል ፈተና ላይ ስልክ ይዘው በገቡ ተማሪዎች አማካይነት ከፈተና ጣቢያ ውጪ ካሉ ልጆች ጋር መልስ እየተላላኩ ነበር። ይህንን ጉዳይ እኛም አንዳንድ ግሩፖች ላይ አይተናል። ቁጥጥራችሁ እስከምን ድረስ ነው? ስልክ ይዘው የሚገቡ ተማሪዎችንስ በዚህ ልክ ፈር የለቀቀ ስራ መስራት ይገባል ወይ? "

አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ :
" እንደ አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ፈተናው ከትምህርት ሚኒስቴር በተሰጠው መመሪያ መሰረት በጥንቃቄ እንዲሰጥ እና ከኩረጃ እና ከመሳሰሉት ነገሮች ነጻ እንዲሆን በተቻለን አቅም ሁላ እየሰራን ነው። ምናልባት ከከተማዋ ውጪ ባሉ የክልል ፈተና ጣቢያዎች አሁን አንቺ ያልሺኝ ጉዳይ ተከስቶ ይሆናል እንጂ ስልክ ወደ ፈተና ጣቢያ ይዘው እንስኪገቡ የሚያስችል አሰራር በየትኛውም የአዲስ አበባ ከተማ ፈተና መስጫ ጣቢያዎች እንደሌለ ግን በጣም እርግጠኛ ሆነን መናገር እንችላለን። "



ትናንትና የጠዋት ፈተና ከተጠናቀቀ በኋ ጀምሮ ከተፈታኝ ተማሪዎች ከላይ የተባለውን ጉዳይ አስመልክቶ በጣም ተሰጋጋሚ ቅሬታ ሲላክልን ነበር፡፡ ይሁንና የሌሎችን ተማሪዎች የፈተና ሳይኮሎጂ ላለመረበሽ ቅሬታቸውን አልለጠፍነውም ነበር።

ወደ አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በአንድ አድሚናችን አማካኝነት ደውለን የተሰጠን ምላሽም ከላይ ያለው ነው። ይሁንና በአንዳንድ ክልሎች ዘንድ ያለው የፈተና አሰጣጥ ሂደት ግን ካቻምና ከነበረው ያልተለየ እንደሆነ ከምናየው አንጻር ታዝበናል።

የፈተናው አሰጣጥ ፍትሐዊ መሆን አለበትና ስለተማሪ የምትጨነቁ ከሆነ በተገቢው መንገድ ይሰጥ ዘንድ የኛም ጥያቄ ነው

Team: @NATIONALEXAMSRESULT