🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

' ከፍተኛ ቁጥር ያለው ቅሬታ እየቀረበ ነው። ይህንን ተከትሎ ግን ' ፈተናው ይሰረዛል ፥ ወደሌላ | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

" ከፍተኛ ቁጥር ያለው ቅሬታ እየቀረበ ነው። ይህንን ተከትሎ ግን " ፈተናው ይሰረዛል ፥ ወደሌላ ቀን ይዘዋወራል …" የሚሉ ከየት እንደመጡ የማይታወቁ መረጃዎች ተማሪዎችን ግራ እያጋቡ ነው፡፡ እንዲህ ያለ ውሳኔ አልተወሰነም፡፡ ለመወሰንም አልታሰብም። ስለዚህ ተፈታኝ ተማሪዎች የቀሩትን 2 የፈተና ቀኖች በእርጋታ ሆነው ሳይረበሹ ሊጨርሱ ይገባል። ምናልባትም አሁን ላይ በተጋነነ ደረጃ ሆነ እንጂ በስልክ የፈተና መልስ መሰጣጠት ከዚህም በፊት የነበረ ነው። ከዚህ በፊትም እንዲህ ሲያደርጉ የተያዙ ተማሪዎች አሉ። አሁንም ቴሌግራም በሚባለው ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያለ አንድ ግሩፕ እንደተዘጋ መረጃው አለን። ስለዚህ ቀሪዎቹ ተማሪዎች ተረጋግተው ሊፈተኑ ይገባል። ትናንትና እንደነገርኩሽ በኛ በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በተቻለን አቅም ይህ አይነት ጉዳይ እንዳይከሰት እየጣርን ነው። "

ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ጋር አድሚናችን ( admin 4) ለሁለተኛ ቀን በስልክ ከነበራት ቆይታ የተወሰደ።



የኛ ሀሳብ:

ኢትዮጲያ ቼክ ለትምህርት ሚኒስቴር "ኢንተርኔት ይዘጋል ወይ" ብሎ በጠየቀበት ወቅት " ይህ አይነት አሰራር የድሮ አሰራር ነው" አይነት ምላሽ የሰጠው ትምህርት ሚኒስቴር እንዲህ አይነት በጠራራ ፀሐይ የሚፈጸም የፈተና ስርቆት እና ኩረጃ ለ2 ተከታታይ ቀናት ሲፈጸሙ ዝምታን መርጧል፡፡

በእርግጥም መልስ ሲዘዋወርባቸው ከነበሩ የቴሌግራም ግሩፖች ውስጥ አንዱ ተዘግቷል፡፡ ጥያቄው ግን ስልክ ተይዞ እንዳይገባ ፥ ፈታኞችም ሆኑ ተፈታኞችም በሕጉ መሰረት ፈተናውን እንዲያየጠናቅቁ መከታተል እንጂ ግሩፕ ማሳደድ ነው ወይ የሚያዋጣው? ለ4 ቀናት የቴሌግራም እና የFB አገልሎትን መያዝስ ቀላል ከጉዳቱ ጥቅሙ አያመዝንም፡ ነበር ወይ? ነው።

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT