Get Mystery Box with random crypto!

የአስትራዜንካ ክትባት ጥቅም ላይ እንዳይውል ያገዱ ሀገራት 7 ደረሱ! ኔዘርላንድ የደም መርጋት የ | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

የአስትራዜንካ ክትባት ጥቅም ላይ እንዳይውል ያገዱ ሀገራት 7 ደረሱ!

ኔዘርላንድ የደም መርጋት የጤና ችግር ያስከትላል ስትል የአስትራዜኒካ የኮሮና ቫይረስ የክትባት መድሃኒት ጥቅም ላይ እንዳይውል አግዳለች፡፡ የኔዘርላንድ መንግስት ለቀጣዮቹ 15 ቀናት የክትባት መድሃኒት እንደማይሰጥም አስታውቋል፡፡ከኔዘርላንድ አስቀድማ አየርላንድ ፣ በኖርዌይ በአንድ ጎልማሳ ላይ የክትባት መድሃኒቱ የደም መርጋት የጤና እክል በማስከተሉ የአስትራዜኒካ ክትባት እንዳይሰጥ ወስናለች፡፡ከኔዘርላንድ እና አየርላንድ በተጨማሪ ዴንማርክ ፣ ኖርዌይ ፣ ቡልጋሪያ ፣ አይስላንድ እና ታይላንድ የአስትራዜኒካ ክትባት ጥቅም ላይ እንዳይውሉ አግደዋል፡፡

አስትራዜኒካ በበኩሉ ደም ያረጋል የሚለው መረጃ ምንም ማረጋገጫ የሌለው ሲል አስተባብሏል፡፡በአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት እና በእንግሊዝ 17 ሚሊዮን ሰዎች የአስትራዜኒካን ክትባት መውሰዳቸው ተሰምቷል፡፡የአስትራዜኒካ የህክምና ዋና ሓላፊ 17ሚሊዮን ሰዎች ክትባቱን ወስደው ከ 100 ያነሱ ሰዎች ላይ ብቻ የደም መርጋት ተከስቷል መባሉን ተከትሎ የቫይረሱ ባህሪ እንደ ግለሰቡ የጤና ሁኔታ ሊለያይ ይችላል፡፡

Bisrat FM

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT